ዉይይት፤ የኢሕአዴግ ዉሳኔና የኢትዮጵያ እዉነታ | ኢትዮጵያ | DW | 31.03.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ዉይይት፤ የኢሕአዴግ ዉሳኔና የኢትዮጵያ እዉነታ

ገዢዉ ፓርቲ የነደፈዉ የአምሥት ዓመት የልማት መርሐ-ግብር በተያዘለት ጊዜ ተግባራዊ መሆኑ በሚያጠያይቅበት፥ የኢትዮጵያ መንግሥት በሰብአዊ መብት ረገጣ ከፍተኛ ወቀሳ በሚሰነዘርበት ወቅት የተካሔደዉ ጉባኤ ያሳለፋቸዉ ዉሳኔዎች ይዘትና ገቢራዊነት ሌላ ጥያቄ ማስነሳታቸዉ አልቀረም።

የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ኢሕአዴግ ካለፈዉ ቅዳሜ እስከ ማክሰኞ ባደረገዉ ዘጠነኛ ጉባኤዉ የቀድሞዉን የፓርቲዉን እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር የአቶ መለስ ዜናዊን የፖለቲካ፥ የልማትና የመልካም አስተዳደር መሮሆችን ገቢር ለማድረግ ወስኗል።ገዢዉ ፓርቲ የነደፈዉ የአምሥት ዓመት የልማት መርሐ-ግብር በተያዘለት ጊዜ ተግባራዊ መሆኑ በሚያጠያይቅበት፥ ኢትዮጵያ መንግሥት በሰብአዊ መብት ረገጣ ከፍተኛ ወቀሳ በሚሰነዘርበት ወቅት የተካሔደዉ ጉባኤ ያሳለፈቸዉ ዉሳኔዎች ይዘትና ገቢራዊነት ሌላ ጥያቄ ማስነሳታቸዉ አልቀረም። በዉይይቱ ከተነሱ ሐሳቦች የሚከተሉት ይገኙበታል። ውይይቱን ካደመጣችሁ በኋላም አስተያየታችሁን በsms ላኩልን። አስተያየታችሁን የምትልኩበት የአጭር መልዕክት መቀበያ ስልክ ቁጥራችን የሚከተለው ነው። 00 49 17 22 66 69 44 ነው። አስተያየቶቻችሁን ፃፉልን፤ መልሰን ለዓየር እናበቃዋለን።

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic