ዉይይት፣ የትግራይ ምርጫ | ኢትዮጵያ | DW | 06.09.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ዉይይት፣ የትግራይ ምርጫ

ማስጠንቀቂያ፣አፀፋዉ ዉዝግብ፣ መወቃቀሱ፣ ሁለቱን ወገኖች ለማግባባት የተሞከረዉ ሽምግልናም እስካሁን ያመጣዉ አግባቢ ዉጤት የለም።የትግራይ ክልል ምርጫም የፊታችን ሮብ ሊደረግ  ዝግጅቱ ተገባድዷል።እንደሰማነዉ ምርጫዉ ለትግራይ ክልላዊ ምክር ቤት ብቻ እንጂ ለወረዳና ለፌደራሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚደረግ አይደለም

አውዲዮውን ያዳምጡ። 31:01

የትግራይ ምርጫ፣ የፌደራዊ መንግስቱ ተቃዉሞና ዉዝግቡ

የኢትዮጵያ ፌደራዊ መንግስትን እና የትግራይ መስተዳድርን ከሥልጣን ሽኩቻ፣ እስከ ገዢ ፓርቲ አደረጃጀት፣ ከተጠርጣሪዎች መታሰር እስከ ፀጥታ ማስከበር ሁለት ዓመት ያነታረከዉ ዉዝግብ  በምርጫ መደረግ እና አለመደረግ ልዩነት ክርሮ እንደቀጠለ ነዉ።ዘንድሮ ለነሐሴ ተይዞ የነበረዉ ብሔራዊ ምርጫ በኮሮና ተሕዋሲ ስርጭት ሰበብ እንዲራዘም የፌደራሉ መንግስትና ምክር ቤቶች ወስነዋል።

የትግራይ ገዢ ፓርቲ ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት) እና የክልሉ መስተዳድር ግን ለምርጫዉ መራዘም የተሰጠዉን ምክንያት ዉድቅ አድርገዉ በክልሉ ምርጫ ለማድረግ ዝግጅታቸዉን አጠናቅቀዋል።የፌደራሉ መንግስት በተለይም የፌደሬሽን ምክር ቤት የትግራዩን ምርጫ «ሕገ ወጥ» በማለት የትግራይ መስተዳድር የምርጫዉን ዝግጅት እንዲያቆም ማስጠንቀቂያ አከል መግለጫ አዉጥቶ ነበር።የትግራይ ክልል ምክር ቤት ግን የፌደረሹን ምክር ቤት ማስጠነቀቂያ ዉድቅ አድርጎታል።

ማስጠንቀቂያ፣አፀፋዉ ዉዝግብ፣ መወቃቀሱ፣ ሁለቱን ወገኖች ለማግባባት የተሞከረዉ ሽምግልናም እስካሁን ያመጣዉ አግባቢ ዉጤት የለም።የትግራይ ክልል ምርጫም የፊታችን ሮብ ሊደረግ  ዝግጅቱ ተገባድዷል።እንደሰማነዉ ምርጫዉ ለትግራይ ክልላዊ ምክር ቤት ብቻ እንጂ ለወረዳና ለፌደራሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚደረግ አይደለም።አንድ መቶ ዘጠና መቀመጫዎች ላሉት ለትግራይ ክልላዊ ምክር ቤት የገዢዉን ፓርቲ የሕወሓትን ጨምሮ የአምስት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮችና አራት የግል ዕጩዎች

ይወዳደራሉ።ከ2.7 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ተመዝግቧል።ኢትዮጵያ ምርጫን ካወቀች ወዲሕ አንድ ክልል ከፌደራሉ መንግስት እዉቅና ዉጪ ምርጫ ሲያደርግ የሮቡ የመጀመሪያዉ ይሆናል።ከፌደራሉ መንግስት ጋር ያለዉ ዉዝግብ፣ የምርጫዉ ዝግጅት እና የሕዝቡ ተሳትፎ ያጭር ዉይይታችን ትኩረት ነዉ።

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic