ዉይይት፤ ኢትዮጵያ ሥጋት እና ተስፋ | ኢትዮጵያ | DW | 04.03.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ዉይይት፤ ኢትዮጵያ ሥጋት እና ተስፋ

የመንግሥትን እርምጃ እና የሕዝቡን የተቃዉሞ ፅናት የሚያነፃጽሩ የፖለቲካ ተንታኞች ገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግ ሐገሪቱ የገጠማትን ችግር ለማስወገድ ከእንግዲሕ መፍትሔ ሊያመጣ አይችልም ይላሉ። ሌሎች ደግሞ የሐገሪቱ ፖለቲካዊ ሁነት እና የወደፊቱን ሒደት አስጊ ይሉታል። ለሌሎች ግን የለዉጥ ተስፋ፤ ለብዙዎች ግራ አጋቢ እና አጠያያቂም ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 30:14

ኢትዮጵያ በለዉጥ ጎዳና ወይስ በስጋት ጠርዝ ላይ

የኢትዮጵያ ዉስጥ በተለይ በኦሮሚያ እና በአማራ መስተዳድሮች የተቀጣጠለዉን ሕዝባዊ ተቃዉሞ ለማርገብ የሐገሪቱ መንግስት ወይም ገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግ ጥልቅ ተሐድሶ ካለዉ ዕቅድ እስከ ካቢኔ ሹም ሽር፤ ከማስተር ፕላን ስረዛ፤ አስር ሺዎችን አፍሶ እስከማሰር፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከመደንገግ፤ እስረኞችን እስከ መፍታት፤ የክልል መስተዳድር መሪዎችን ከመቀየር መገናኛ ዘዴዎችን በተለይም የኢንተርኔት አገልግሎትን እስከ መዝጋት የሚደርሱ እርምጃዎችን ወስዷል።

በቅርቡ ደግሞ ከዚህ ቀደም የተወሰዱ እርምጃዎችን ዳግም እያመነዠኸ ወይም ሪሳይክል እያደረገ ነዉ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዳግም መደንገግ፤ የኢንተርኔት አገልግሎት መዝጋት፤ በካቢኔ፤ በኦሮሚያና በትግራይ መስተዳድር የተደረጉ ሹም ሽሮች በፌደራሉ ጠቅላይ ሚንስትር ሥልጣን መልቀቅ ማጠናከር የዳግም እርምጃዎቹ አብነቶች ናቸዉ።

ሕዝባዊ አመፅ እና ተቃዉሞ ግን አልቆመም። የመንግሥትን እርምጃ እና የሕዝቡን የተቃዉሞ ፅናት የሚያነፃጽሩ የፖለቲካ ተንታኞች ገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግ ሐገሪቱ የገጠማትን ችግር ለማስወገድ ከእንግዲህ መፍትሔ ሊያመጣ አይችልም ይላሉ። ሌሎች ደግሞ የሐገሪቱ ፖለቲካዊ ሁነት እና የወደፊቱን  ሒደት አስጊ ይሉታል። ለሌሎች ግን የለዉጥ ተስፋ፤ ለብዙዎች ግራ አጋቢ እና አጠያያቂም ነዉ። የስጋት፤ ተስፋ፤ የማጠያየቁ ምክንያት የዛሬዉ ዉይይታችን ትኩረት ነዉ።

ነጋሽ መሐመድ

 

Audios and videos on the topic