ዉይይት፤ አጠያያቂዉ የኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት  | ኢትዮጵያ | DW | 23.07.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ዉይይት፤ አጠያያቂዉ የኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት 

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፉት ተከታታይ ዓመታት ትምህርትን ለማስፋፋትበሚያደርገዉ ጥረት በርካታ ትምህርት ቤቶችን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በየአካባቢዉ ከፍቶአል። ይሁን እንጂ አስተማሪዎች በቂ እዉቀትን ስለመስጠታቸዉ አጠያያቂ ስለመሆኑ አንድ በቅርቡ ይፍ የሆነ ጥናት አሳይቶአል፤ የተማሪዎችም እንዲሁ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 29:19

«የአስተማሪዎች ሥነ-እዉቀትም አስደንጋጭ መሆኑን በጥናት አረጋግጠናል»ተወያዮች

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፉት ተከታታይ ዓመታት ትምህርትን ለማስፋፋትበሚያደርገዉ ጥረት በርካታ ትምህርት ቤቶችን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በየአካባቢዉ ከፍቶአል። እንደ ጎርጎረሳዊዉ አቆጣጠር እስከ 2015 ሥራ ላይ የነበረዉ የተመድ የአምዓቱ የልማት ግብ «UNDP» አማካኝነት የተገኘ ገንዘብንም ሆነ ከሃገሪቱ የሚመደብ በጀትን በመጠቀም መንግሥት ያስገኛቸዉ የትምህርት ተቋማት በየደረጃዉ የሚገኘዉን የተማሪ ቁጥር በእጅጉ እንደሚጨምር አድርገዋል። በተለይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በየክልሉ በየዓመቱ ከኮሌጅና ከዩንቨርስቲ ትምህርቱን አጠናቆ የሚወጣዉ ተማሪ በ 100 ሺህ ይቆጠራል። ዘንድሮ ብቻ የመንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብቻ ከ 125 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስመርቀዋል። የግል ኮሌጅና ዩንቨርስቲዎች ያስመረቅዋቸዉ ተማሪዎች ሲታከሉበት 150 ሺህ ይበልጣል ተብሎ ይገመታል። መንግሥት ትምህርትን በማስፋፋት ረገድ ያደረገዉ ጥረት የተማሪዎችን ቁጥር በማሳደጉ የሚያመሰግኑ ብዙዎች ናቸዉ። የዛኑ ያክል የትምህርት ጥራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ መምጣቱ ብዙዎችን የሚያሰጋ ጉዳይ ሆንዋል። በቅርቡ ይፋ የሆነዉ ጥናት እንደጠቆመዉ ደግሞ የመምህራን እዉቀት አጠያያቂ ነዉ። ይህ ዉይይታችን የትምህርት ጥራትና መፍትሄዉን ይቃኛል።  በዉይይቱ ከተነሱት ነጥቦች መካከል ተከታዩ ይገኝበታል። በዉይይቱ ላይ ዶክተር መክብብ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መምህርና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ከእንጊሊዙ ዱርሃም ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በሚካሄደዉ «የኢትዮጵያ የሳይንስ ሥነ-ትምህርት ጥናት» ቡድን መሪ።  ዶክተር አብርኃ ኪሮስ የትግራይ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ። ዶክተር ዳኛቸዉ አሰፋ በአዲስ አበባ ዪኒቨርስቲ የቀድሞ ፍልሰፍና መምህር እንዲሁም፤ መምህር ስዩም ተሾመ ከአምቦ ዩኒቨርስቲ ወሊሶ ካምፓስ አስተማሪና የድረ-ገፅ ፀሐፊ ናቸዉ። የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ሙሉ ዉይይቱን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን። 

አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic