ዉይይት:-ሥጋትና ተስፋ ያጠላበት የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ለዉጥ | ኢትዮጵያ | DW | 24.03.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ዉይይት:-ሥጋትና ተስፋ ያጠላበት የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ለዉጥ

መንግሥት ሃገሪቱን «ለዉጡን» ከየት ተነስቶ የት መድረስ እንደሚፈልግ ፍኖተ ካርታ አስቀምጦ ለሕዝብ ግልፅ መደረግ አለበት። ከኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ምን ይጠበቃል? ምን ማድረግ ነዉ የምንፈልገዉ የሚለዉ ለሕዝብ በግልፅ ይቀመጥ። ለዉጡ የተገነባዉ አሸዋ ላይ ሳይሆን ኮንክሪት ላይ ነዉ። ለዉጡን መቀልበስ አይቻልም» ተወያዮች የሰነዘሩት ኃሳብ

አውዲዮውን ያዳምጡ። 31:30

«የኢትዮጵያ ሕዝብ ተቻችሎ መኖር ያዉቅበታል፤ ችግሩ ያለዉ ልሂቃኑ ጋር ነዉ»

በኢትዮጵያ ለዉጥ ከጀመረ አንድ ዓመት ሊሞላዉ ነዉ። በዚህ ለዉጥ የተገኙ  በርካታ ፍሪዎች መጠቀሳጠዉን ያህል የለዉጥ ተስፋ የደበዘዘ መስሎ መታየቱን ብዙዎች ይናገራሉ።  በሃገሪቱ እዚህም እዚያም የተከሰተዉ የዜጎች መፈናቀል፤ በዘር እና በብሔር ጎራ ለይቶ መወዛገብ ፤ በኢህአዴግ  አባል ድርጅቶች መካከል በጥርጣሪ መተያየት እና ይህን ተከትሎ  የሚመሩዋቸዉ ክልሎች እርስ በርስ መወዛገብ፤ ሕገወጥ ተብሎ የሚፈርሱ ቤቶችና የሚፈናቀሉ ዜጎች መበራከት እንዲሁም የማእከላዊ መንግሥት መዳከም ለዉጡን ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ  ምናልባትም ሃገሪቱን ወደ ብጥብጥ ይወስዳታል ብለዉ የሚሰጉ ጥቂቶች አይደሉም።  በሌላ በኩልም መንግሥት በሰላም ለሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን እንዲሁም በቀጣይ የፖለቲካ ምህዳሩን  ይበልጥ በማስፋት መጭዉ  አገር አቀፍ ምርጫ ነጻ እና ተአማኒነት ባለው መልኩ እንዲከናወን አስፈላጊውን ጥረት እያደረኩ ነው ሲል በተደጋጋሚ ይነገራል።  ሥጋት ኀስፋ ያጠላበት የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ለዉጥ በሚል በዉይይት የተሳተፉና ኃሳባቸዉን ያካፈሉን ፤ መምህርት መዓዛ መሐመድ፤ የኢትዮጵያዉያን ሃገራዊ ንቅናቄ ፓርቲ አባል፤ አቶ ኦልባና ሌሊሳ፤ የቀድሞ እስረኛ እና የኦሮሞ ፖለቲካ አቀንቃኝ፤ አቶ አበበ አካሉ፤ የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ እና የቀድሞ እስረኛ እንዲሁም ፤ አቶ ገረሰፉ ቱፋ፤  የፖለቲካ አቀንቃኝ ናቸዉ ። ተወያዮችን በዉይይቱ ስለተካፈሉ በ «DW» ስም እያመሰገንን ፤ ሙሉ ዉይይቱን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።  


አዜብ ታደሰ   
ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች