ዉይይት፣ መራሩ ትግልና ዉጤቱ | ኢትዮጵያ | DW | 12.05.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ዉይይት፣ መራሩ ትግልና ዉጤቱ

አሁን የተደረገዉ የስልጣን ሽግግር ወይም ለዉጥ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን የረጅም ዘመን የመብት ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ይመልሳል ብሎ የሚጠብቅ የለም።በስልጣን ሽግግሩ መላዉ ሙስሊም ተደስቷል ብሎ ማሰብም የዋሕነት ነዉ።ይሁንና ሠላማዊ የስልጣን ሽግግር በማይታወቅባት ኢትዮጵያ ሙስሊሞች ለሠላማዊ የስልጣን ሽግግር መብቃታቸዉ ብዙዎችን ያረካ መስሏል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 30:16

ዉይይት፣ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተስፋ

ለዛሬዉ ዉይይት ፣ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ትግል፣ ሒደትና ዉጤቱ የሚል ርዕሥ ሰጥተነዋል።እንደተከታተልነዉ ባለፈዉ ሚያዚያ 23 የተሰየመዉ የኢትዮጵያ ዑለማዎች ጉባኤ ጊዚያዊ የዑለማዎች ምክር ቤት መርጧል።ምክር ቤቱ በፋንታዉ የባላደራ  ቦርድ አባላትን መርጧል።

አዲስ የተመረጡት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መሪዎች እስካሁን ድረስ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ጉባኤ ተብሎ የሚጠራዉን ተቋም ይመሩ ከነበሩት ወገኖች ኃላፊነቱን ባለፈዉ ማክሰኞ በይፋ ተረክበዋል።

አሁን የተደረገዉ የስልጣን ሽግግር ወይም ለዉጥ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን የረጅም ዘመን የመብት ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ይመልሳል ብሎ የሚጠብቅ የለም።በስልጣን ሽግግሩ መላዉ ሙስሊም ተደስቷል ብሎ ማሰብም የዋሕነት ነዉ።ይሁንና ሠላማዊ የስልጣን ሽግግር በማይታወቅባት ኢትዮጵያ ሙስሊሞች ለሠላማዊ የስልጣን ሽግግር መብቃታቸዉ ብዙዎችን ያረካ መስሏል።

ሽግግሩ፣ ሙስሊሞች በተለይ ከ2004 ጀምሮ በተከታታይ ያደረጉት ትግል አንድ ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያረጋግጥም ነዉ።ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ለእምነት ነፃነት መከበር ለተከታታይ ዐመታት ያደረጉት ትግል የተገደሉ፣ የታሰሩ፣የተገረፉ፣የተሰደዱበት ግን ፍፁም ሠላማዊ ነበር።የትግሉ ሒደት፣ አሁን የተገኘዉ ዉጤትና አስተምሕሮቱ የዛሬ ዉይይታችን ትኩረት ነዉ።

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic