ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሣ ፣ ምኅረት ያገኙበት ይቅርታ፣ | ኢትዮጵያ | DW | 07.10.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሣ ፣ ምኅረት ያገኙበት ይቅርታ፣

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀ መንበር የወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ከእስር መለቀቅ በብዙዎች ዕይታ ሠናይ ክሥተት ነው ።

default

በሌላ በኩል፣ ውሳኔው የራሳቸው ቢሆንም፣ የተለቀቁበት ሁኔታ እና የወደፊት የፖለቲካ እጣ- ፈንታቸው ማነጋገሩ አልቀረም ። በዚህ ጉዳይ፣ ተክሌ የኋላ፣ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ምክትል ሊቀምንበርንና አንድ የህግ ባለሞያ አነጋግሮ ተከታዩን ዘጋባ አጠናቅሯል።

የአንድነት ለፍትኅና ዴሞካራሲ ፓርቲ ሊቀ-መንበር፣ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ አንድ ዓመት ከ 9 ወር ገደማ ፣ ዳግመኛ የአሥራት ዘመን ካሳለፉ በኋላ፣ ትናንት በመፈታታቸው ፤ ከቤተሰብ ፤ ዘመድና ወዳጆቻቸው ሌላ፤ የፓርቲያቸው አባላት ፣ በአገር ውስጥና በውጭ የሚደግፏቸውና የሚያደንቋቸው ኢትዮጵያውያን ፣ የውጭ ሰዎች ጭምር እፎይታ ነው የተሰማቸው። የተፈቱበት ፣ ወይም ይቅርታ ጠየቁ የተባለበት ደብዳቤና ራሳቸው በቃል የሰጡት ማብራሪያ ግን ማነጋገር ይዟል። የይቅርታ መጠየቂያውን ደብዳቤ የተመለከተው የራሳቸው ፓርቲ እንዴት ነው የሚተረጉመውም ሆነ የሚመለከተው!? --የአንድነት ለፍትኅና ዴሞካራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር ፣ ኢንጂኔር ግዛቸው ሽፈራው--

(ድምፅ)—

ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሣ ከ 1997 የግንቦት ምርጫ በኋላ በተፈጠረው ውዝግብ ሳቢያ ከቅንጅት ለአንድነትና ዴሞክራሲ የአመራር አባላት ጋር ወህኒ ከወረዱ በኋላ በመጨረሻ ይቅርታ ጠይቀው መፈታታቸውን የካዱበት ጊዜ አልነበረም። የይቅርታ አጠያየቁ ሂደት ግን ደንብን የተከተለ እንዳልነበረ አስረድተው፣ በዚህ ነጥብ ዙሪያ በሥልጣን ላይ ካለው መንግሥት ጋር በተፈጠረ እሰጥ-አገባ ሳቢያ ፤ ዳግመኛ ለእሥራት መዳረጋቸው የታወቀ ነው። የአሁኑ የይቅርታ አጠያየቅ፣ ያለፈው የይቅርታ አጠያየቅ ትክክለኛ አልነበረም ያሉትን የሚሽርና ትክክለኛ ነበረ! የሚያሰኝ ነው? ጉዳዩ ፣ በህግ ባለሙያ እንዴት ይታያል? ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ---

(ድምፅ)---------

የአንድነት ለፍትኅና ዴሞክራሲ ፓርቱ ሊቀመንበር ተመልሰው የኃላፊነት ቦታቸውን ይዘው፣ ፓርቲውን ለመምራት ያሳዩት ዝንባሌ እስከምን ድረስ ይሆን!? ይቅርታ የጠየቁትን ደብዳቤ ለሚመረምር፣ ስለወደፊት ህይወታቸውም በጨረፍታ ከሰጡት መግለጫ በመነሣት ምንድን ነው ሊባል የሚቻለው? --ኢንጂኔር ግዛቸው----

(ድምፅ)----------

ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሣ፣ የፖለቲካ ሰው ቢሆኑም በሙያ የህግ ምሁር ናቸው። አሁን ከእሥራት የተለቀቁበት የይቅርታ መጠየቂያ ደብዳቤና መግለጫቸውም ቢሆን ፤ በወደፊቱ የፖለቲካ ህይወታቸው ምን የሚያስከትለው ሁኔታ ይኖራል ? የህግ ባለሙያ አቶ ወልደ አማኑኤል መሸሻ--

(ድምፅ)

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ