የጎዳና ሥነ-ጥበብ በአዲስ አበባ
የጎዳና ጥበብ
«በቀጣይ የሃረር ግንብ የአክሱም ሃዉልቶች ፤ የላሊበላ ዉቅር ቤተክርስትያናት፤ የጥያ ትክል ድንጋዮች ፤ በባሌ የሚገኘዉ ዋሻ አለ፤ ፋሲለደስ የመሳሰሉ ኢትዮጵያን የሚገልፁ በርካታ ታሪካዊ ቦታዎችም አሉን። ከዚህ በተጨማሪ የኛን ማንነት የሚገልጹ አለባበሶች የፀጉር ሥራዎች፤ የአመጋገብ ሥርዓቶች ሁሉ አሉን። እነዚህን ነገሮች ራሳችን መግለፅ በምንችልበት ሁኔታ ቀለማትንም ጭምር በነዚህ ኮንክሪቶች ላይ እንዲያርፉ እንፈልጋለን።» የአዲስ አበባ የዉበት መናፈሻና ዘላቂ ማረፍያ ልማትና አስተዳደር ተቋም