ወጣት የምልክት ቋንቋ አስተርጓሚና አስተማሪዎች | ባህል | DW | 19.09.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

ወጣት የምልክት ቋንቋ አስተርጓሚና አስተማሪዎች

የዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት የምልክት ቋንቋ ላይ ያተኩራል። ይህንን በተመለከተ ያነጋገርናቸው ሶስት የአካል ጉዳተኛ ያልሆኑ ነገር ግን የምዕልክት ቋንቋን ኢትዮጵያ ውስጥ ተምረው በዚህ ሙያ የተሰማሩ ወጣቶችን ነው።

የምልክት ቋንቋን፣ መስማትየተሳናቸው፣አስተርጓሚዎች ወይም መምህራን ዕለት ከዕለት ይጠቀማሉ። የምልክት ቋንቋ አስተርጓሚ የሆነችው መዓዛ መላኩ ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ሬዲዮ እና ቴለቪዥን ድርጅት ተብሎ ይጠራ በነበረው የአሁኑ «ኢትዮጵያን ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን» መስማት ለተሳናቸው ፕሮግራም ክፍል ውስጥ ባለፉት አምስት አመታት በረዳት አዘጋጅነት ሰርታለች።ከዚህም ሌላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምልክት ቋንቋ አስተርጓሚዎች ማህበርም ፕሬዚዳንት ሆና አገልግላለች። በአሁኑ ሰዓት ለ2ኛ የከፍተኛ ትምህርት ኖርዌይ ሀገር የምትገኘው ወጣት ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚገኙት ፅሙማን ቁጥር ስትናገር እስከ 1,5 ሚሊዮን ሊደርሱ ይችላሉ ተብሎ ይገመታል ትላለች።

Junge Gehörlose in Gaza

የቋንቋው ምልክቶች

ሌላው ያነጋገርናት የምልክት ቋንቋ አስተርጓሚ ሳባ ተስፋዬ ትባላለች። በኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማህበር ውስጥ ታገለግላለች። ከምልክት ቋንቋ ጋር የተዋወቀችው ቤተ ክርስትያን ውስጥ ስታገለግል ነበር። መዓዛ ይህን የምልክት ቋንቋ ትምህርት በከፍተኛ ተቋም ደረጃ ተምራ እንድትጨርስ መሰረት የሆናት፤ ሳባ የተማረችበት ቤተ ክርስትያን እንደሆነ ትናገራለች። ሳባ እና መዓዛ በቤተ ክርስትያን ከቋንቋው ጋር ሲተዋወቁ አንተነህ ሰለሞን ደግሞ ከፍተኛ ተቋም ከገባ በኋላ ነው የተማረው ። አንተነህ ዛሬ ተምሮ በጨረሰበት የጋዜጠኝነት ሙያ ሳይሆን፤ አዲስ አበባ ውስጥ ቪክቶር መስማት የተሳናቸው የተባለ ትምህርት ቤት ውስጥ የምልክት መምህር ሆኖ ያስተምራል።

መስማት የተሳናቸው ኢትዮጵያውያንን በተወሰነ መልኩ በትምህርትም ሆነ በመግባባት ረገድ መርዳት በመቻላቸው ሶስቱም ወጣቶች በስራቸው ደስተኛ ናቸው። ከስራቸው ጋር በተያያዘ መስማት የተሳናቸው ስለሚገጥማቸው ፈተናና። በመማር ማስተማሩ ሂደት ላይ ስላለው ችግር ጨምረው ገልፀውልናል።

ኢትዮጵያ ውስጥ የምልክት ቋንቋን አስመልክቶ አስተርጓሚ እና አስተማሪ የሆኑት ወጣቶችን በዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት ያካፈሉንን ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic