ወጣት ሴቶች በሳውዲ ዓረቢያ | ባህል | DW | 14.09.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ወጣት ሴቶች በሳውዲ ዓረቢያ

በርካታ ኢትዮጵያውያን ሴቶች በየጊዜው የተሻለ ህይወት ፍለጋ ወደ አረብ ሀገር ይጓዟሉ። በርግጥ እዚያ ኢትዮጵያ ውስጥ በቤት ሰራተኝነት ከሚያገኙት የበለጠም ይከፈላቸዋል። ግን፤ ኑሮ በአረብ አገር በጣም ከባድ እንደሆነ፤ በተለይ ሄደው ያዩት በተደጋጋሚ ይናገራሉ።

እጅጋየሁ ደበበ የ 23 አመት ወጣት ናት። በሴቶች ላይ የሚደርሱ ችግሮች ለሌሎች እህቶቼ ላካፍል እፈልጋለሁ ስትል ወደ ዶይቸ ቬለ መልዕክት ላከችልን። በስልክ አነጋግረናታል። እንደ በርካታ ሴት ኢትዮጵያውያን እጅጋየውን ከሀገሯ እንድትወጣ የዳረጋት ችግር ነው። አጀማመሬ ጥሩ ነበር ትላለች። በአርሲ ስሬ ወረዳ እስከ 10ኛ ክፍል ትምህርቷን ተከታተለች። ኋላም ቀጥላ ለመማር የትምህርት ነጥቧ ጥሩ ስላልነበር፤ ወደ ደብረዘይት ከተማ እህቷ ጋ ሄደች። ወደ ሳውዲ እስክትሄድ ድረስ እዛም ስትሰራ እና ስትማር ቆየች።

ውጪ የሚኖሩ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ የራሳቸውን እና የቤተሰባቸውን ህይወት ሲለውጡ ይታያል። ከበስተ ጀርባ ያለው ታሪክ ግን ሌላ ነው ትላለች ወጣቷ፤ በሷ እና በሌሎች ሴቶች ላይ የደረሱ የመድፈር ሙከራዎች በግልፅ አጫውታናለች።

እጅጋየሁ ኢትዮጵያ ሳለች በፅዳት ሰራተኝነት 400 ብር ፤ ሳውዲ አረቢያ ደግሞ 3500 ብር ታገኛለች ። ሲከፋት እና ስታዝን፤ ስሜቷን በግጥም ነበር ከዚህ ቀደም የምትገልፀው።

በአረብ ሀገር ህይወት ከባድ ከሆነ፤ ለምን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ እንዳልሞከረችም ነግራናለች። ከዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሒሩት መለሰ

Audios and videos on the topic