ወጣት መራጮች በጀርመን | ባህል | DW | 20.09.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ወጣት መራጮች በጀርመን

ለመሆኑ በጀርመን ሀገር ወጣቶች እንዴት ለምርጫ ይዘጋጃሉ? የምርጫ ቀን እና ምርጫስ ምን ይመስላል? በዛሬው የወጣቶች ዓለም የምንቃኘው ይሆናል።

የዶይቸ ቬለ ስቱዲዮ በሚገኝበት በዚህ የቦን ከተማ ፤ መንገዶች ሁሉ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በሚያስተዋውቁ የምርጫ ፖስተሮች ተሞልተዋል።የምርጫ ቀን መቃረቡ ለማንም ግልፅ ነው።በጀርመን ሀገር ደንብ መሰረት 18 ዓመት የሞላቸው ወጣቶች የመምረጥ መብት አላቸው። ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ መምረጥ የሚችሉ 3 ሚሊዮን የሚሆኑ ጀርመናውያን የምርጫ ወረቀት ደርሷቸዋል። አብዛኞቹም በመጪው እሁድ በጀርመን አጠቃላይ ምርጫ ይሳተፋሉ። ግን የትኛውን እጩ ተወዳዳሪ እና ፓርቲ እንደሚመርጡ ግራ ነው የተጋቡት። ከጥቂቶቹ አስተያየት ውስጥ ፦

Bildnummer: 60441232 Datum: 06.09.2013 Copyright: imago/Reiner Zensen Berlin, den 06.09.2013 Foto: Großflächenplakat der CDU am Berliner Hauptbahnhof. Unter dem Motto, Deutschland in guten Händen, wirbt die CDU mit einem Großflächenplakat auf dem die typische Handhaltung von Bundeskanzlerin Angela Merkel zu sehen ist, für die Bundestagswahl 2013. People Politik Wahlplakat Plakat Wahl Bundestagswahl xns x0x 2013 quer premiumd POLITIK POLITICS Plakat Wahlwerbung Wahl Bundestagswahl Wahlplakat Partei CDU 60441232 Date 06 09 2013 Copyright Imago Reiner Zensen Berlin the 06 09 2013 Photo Large-size billboard the CDU at Berlin Central Station under the Motto Germany in Good Hands advertises the CDU with a Large-size billboard on the the typical Hand position from Chancellor Angela Merkel to see is for the Federal election 2013 Celebrities politics Election billboard Billboard Choice Federal election xns x0x 2013 horizontal premiumd politics POLITICS Billboard Election campaign Choice Federal election Election billboard Party CDU

መንገዶች ሁሉ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በሚያስተዋውቁ የምርጫ ፖስተሮች ተሞልተዋል።

«አዎ እመርጣለሁ። በአጠቃላይ መምረጥ አስፈላጊ ነው ብዬ አስባለሁ። በሌላ በኩል ደግሞ አስፈላጊነቱ እየቀነሰብኝ መጥቷል። ምክንያቱም ይህ ፓርቲ ወይም ይህን ሰው ነው መምረጥ የምፈልገው የምለው የለኝም።»

« በአሁኑ ሰዓት ገና አልወሰንኩም። ምክንያቱም ባሉን ፓርቲዎች በሙሉ በአሁኑ ሰዓት ደስተኛ አይደለሁም።»

« መምረጤን ርግጠኛ ነኝ። ማን እና ምን እንደሚሆን ግን አሁን ርግጠኛ አይደለሁም። በርግጠኝነት የማውቀው በግራ ካሉት ፓርቲዎች አንዱ እንደሚሆን ነው።»

« ሰዎች ለመምረጥ መሄዳቸው አስፈላጊ ነው። ይሁንና ለውጥ ያመጣል ብዬ አላስብም።»

« ከፓርቲዎቹን አንዱን ለመምረጥ ከባድ ነው። ምክንያቱም የማልፈልገውን ነገር በፕሮግራማቸው አካተዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ሌላው አማራጭ ጭራስ የባሰ ነው ስል አስባለሁ።»

Bildbeschreibung: Stimmzettel Fotograf: Lydia Heller / DW Aufnahmedatum: 2013 Aufnahmeort: Berlin Angeliefert von Lydia Heller am 15.9.2013

የምርጫ ወረቀት

ግራ የተጋቡ ወጣቶች በየቦታው ይስተዋላሉ። ይሁንና የፖለቲካ ፓርቲዎች ከመጪውም በላይ በፌስ ቡክ እና ትዊተር የምርጫ ዘመቻ እያካሄዱ እንደሆነ ይናገራሉ። በምርጫ የሚሳተፉት ሰዎች እድሜ በአማካይ ሲሰላ 45 ነው። አዳዲስ መራጮች በምርጫ ዘመቻው ችላ እንዳይባሉ አንዳንድ የወጣቶች ማህበሮች ወጣቱን የማነቃቃት ስራ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ። የ 25 ዓመቷ ሶፊያ በፕ ከአነቃቂዎቹ አንዷ ናት « እንደሚመስለኝ በርካታ ወጣቶች የፖለቲካ ፍላጎት አላቸው አገራቸው ውስጥ እየተካሄደ ስላለው ነገር ማወቅ ይፈልጋሉ። ይሁንና ስላለው ልዩነት እና በርግጥ ለሀገሪቷ ስለሚጠቅመው ለመለየት ስለሚዳግት ነው።»

ወጣት ኢንጂኒየር ኃይሉ ታደሰ፤ አህን ከተማ በሚገኘው የጀርመን ዮንቨርሲቲ ያገለግላል። ከልጅነቱ ጀምሮ በጀርመን ሀገር ነው የሚኖረው። ዜግነት ወስዶ መምረጥ ከጀመረ አምስት ዓመቱ ነው። እስካሁንም በጀርመን የምክር ቤት ምርጫ እና የክፍለ ሀገር የተለያዩ ምርጫዎች ላይ ተሳትፏል። የአሁኑ እሁድም አንዱ መራጭ ነው። ሌላው እንዲሁ በእሁዱ ምርጫ የሚሳተፈው እስጢፋኖስ ሳሙኤል የሚንት ሚዲያ ኤጀንሲ ባለቤት ነው። በጀርመን ሀገር ስለሚካሄድ የምርጫ ስነ-ስርዓት ገልፀውልናል። ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic