ወደ ኢትዮጵያ የሚላከው ገንዘብ እና ጥቁሩ ገበያ | ኤኮኖሚ | DW | 06.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

ወደ ኢትዮጵያ የሚላከው ገንዘብ እና ጥቁሩ ገበያ

በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ አገር ቤት የሚልኩት የገንዘብ መጠን መጨመሩን የዓለም ባንክ በቅርቡ ባወጣው ዘገባ አስታውቋል። በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ግን ሁልጊዜም ገንዘብ የሚልኩት በህጋዊ መንገዶች አይደለም።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:07
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
10:07 ደቂቃ

ጥቁሩ ገበያ

በዓለም ባንክ የናሙና ጥናት መሰረት 39 በመቶ ኢትዮጵያውያን በውጭ አገራት የሚኖር ቤተሰብ አሊያም ወዳጅ ዘመድ አላቸው። ከእነዚህ መካከል 18 በመቶው ከእነዚሁ ወዳጅ ዘመዶቻቸው በቋሚነት ገንዘብ ይላክላቸዋል። ገንዘብ ተቀባዮቹ በአማካኝ 120 ዶላር በአመት ለአምስት ጊዜ ያገኛሉ።(600 ዶላር ማለት ነዉ።) ሁለት ሚሊዮን ገደማ የሚገመቱት ዉጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ አገር ቤት የሚልኩት ገንዘብ እስከ ጎርጎሮሳዊው 2010 ድረስከጠቃላዩ አመታዊው የምርት መጠን (GDP) ያለው ድርሻ 2% ብቻ ሆኖ ቆይቷል። የዓለም ባንክ ባለፈው የጎርጎሮሳውያኑ አመት መገባደጃ ባወጣው ዘገባ ግን ከሰሐራ በርሐ በታች ከሚገኙ አገራት በውጭ አገራት ከሚኖሩ ሰዎች የሚላክ ከፍ ያለየገንዘብ መጠን በማግኘት ኢትዮጵያ እና ኬንያ ቀዳሚ መሆናቸውን አትቷል።

ከውጭ አገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚላከው የገንዘብ መጠን በሚቀጥሉት ሶስት አመታት በ50 በመቶ እድገት እንደሚያሳይም የዓለም ባንክ ጨምሮ አትቷል። አቶ ተወልደ የጠቀሷቸው የአውሮጳ እና የሰሜን አሜሪካ አገራት ከገጠማቸው የኢኮኖሚ ቀውስ ማገገም ለኢትዮጵያውያ መልካም ዜና ሳይሆን አይቀርም። በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ መቀነስም በውጭ አገራት ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ፋታ ሆኖ ወደ አገር ቤት ዳጎስ ያለ ገንዘብ የመላክ እድል ፈጥሯል።

የዓለም ባንክ በቅርቡ ይፋ ባደረገው እና የመኖሪያ ቀያቸውን ጥለው በመላው ዓለም የተበተኑ ሰዎች ወደ አገሮቻቸው ከላኩት601ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 441ቢሊዮን ዶላሩ ወደ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያን መሰል ታዳጊ አገሮች መሄዱን አሳይቷል። ከታዳጊ አገራት የተሰደዱ ሰዎችን «ጥንቁቅ ቆጣቢ» ያሉት የዘገባው ተባባሪ አዘጋጅ ዲሊፕ ራታ የገንዘብ መጠኑ ታዳጊዎቹ አገሮች በሰብዓዊ እርዳታ ከሚያገኙት በሶስት እጥፍ የሚልቅ እንደሆነ ተናግረዋል። ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉት በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ አገር ቤት የሚልኩት የገንዘብ መጠን ለበርካታ አመታት አገሪቱ በውጭ ንግድ ከምታገኘው የሚበልጥ እንደነበር አቶ ጌታቸው ይናገራሉ።

ነዋሪነታቸውን በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ያደረጉት አቶ ሙከሚል አምዲኖ በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ገንዘብ የሚልኩባቸውን መንገዶች ተመልክተዋል። አቶ ሙከሚል በባንክ እና የኃዋላ አገልግሎት አቅራቢ የገንዘብ ተቋማት ወደ ኢትዮጵያ ከሚላከው ይልቅ ሌላ መንገድ እያደገ መምጣቱን አስተውለዋል።

በዋሽንግተን ከተማ የሚኖሩት አቶ ውብሸት መሐሪ ጊዮን ፋይናንሺያል የተሰኘ የአካውንቲግ እና ፋይናንስ ተቋም መስራች እና ባለቤት ናቸው። እርሳቸውም በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተሻለ ምንዛሪ ፍለጋ ገንዘባቸውን ወደ አገር ቤት እንደሚልኩ ይናገራሉ።

በመንግስት እና በፋይናንስ ተቋማት ውስን ተሳትፎ ቁጥጥር የሚደረግበት የውጭ ምንዛሪ ግብይት የአቅርቦት እና ፍላጎት አለመጣጣም ይታይበታል።

አቶ ሙከሚል ከአንድ ሺ ዶላር በላይ የሆነ ገንዘብ በባንክ እና የኃዋላ አገልግሎት አቅራቢ የገንዘብ ተቋማት ይልቅ በጥቁር ገበያ ተሳትፎ በሚያደርጉ ግለሰቦች መላክ እየተለመደ መምጣቱን ይናገራሉ። ገንዘብ ሰብሳቢዎቹም አንድም ወደ ኢትዮጵያ መግባት የነበረበትን የውጭ ምንዛሪ ያስቀሩታል አሊያም በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ጥቁሩ ገበያ ያስገቡታል።

ለአቶ ጌታቸው ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከፍተኛ እድገት እያሳየ የመጣው የጥቁር ገበያ በኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ አደጋ ሊደቅን እንደሚችል ስጋት አላቸው።

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic