ወደ ሳውዲ አረቢያ ዳግም ስደት | ባህል | DW | 11.04.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

ወደ ሳውዲ አረቢያ ዳግም ስደት

ማንኛውንም መንገድ ተደቅመው ዳግም ወደ ሳውዲ አረቢያ የሚሰደዱ ወጣት ኢትዮጵያንኖች ባለፈው ህዳር ወር የሳውዲ ዓረቢያ መንግሥት በሀገሪቱ የሚገኙ ህገ ወጥ የሚለውን ስደተኞች እያሰረ ከሀገር ሲያባርር፤

ከ150 000 በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በግዳጅ አልያም በፍቃደኝነት ወደ ሀገራቸው እንደተመለሱ ይታወሳል። ይሁንና ይህ ከሆነ ከአምስት ወር በኋላ መልሰው ለደላላ እየከፈሊሉ ወደ ሳውዲ አረቢያ የሚያመሩ አልጠፉም።

ትክክለኛ ስሟ እንዳይጠቀስ የፈለገችውን ወጣት ለጊዜው ኤልሳ ብለን እንጥራት። ወጣቷ ከአምስት ወር በፊት ከሪያድ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አንዷ ናት። ኤልሳ ጥቂት ወራት ኢትዮጵያ እንደቆየች ተመልሳ ለደላሎች ገንዘብ ከፍላ ከኢትዮጵያ ለመውጣት ወሰነች። ከአንድ ሳምንት በፊትም ተመልሳ ሪያድ ገባች። በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው በገቡበት ወቅት አገር ጥላ የወጣችበትን ምክንያት ገልፃልናለች።

እንደ ኤልሳ ምንም ተስፋ ያልታየው ሌላው ያነጋገርነው ወጣት ሞገስ በሉኝ ብሏል። እሱም ከአምስት ወር በፊት ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱት አንዱ ነው። ወደ ሳውዳ አረቢያ የተመለሰው ለደላላ ገንዘብ ከፍሎ ነው። ከሀገር እና ከቤተሰብ ርቀው መኖሩን ፈልገው እንዳልሆነ እና ኑሮዋቸውም አድካሚ እንደሆነ ሁለቱም ይናገራሉ። ይሁንና ሌሎችም ስራ እስካላገኙ ድረስ፤ ኤልሳ እንደምትለው መልሰው መሰደዳቸው አይቀሬ ነው።

Äthiopische Flüchtlinge in Saudi

ኤልሳ ተመልሳ ሪያድ እስክትገባ አንድ ወር ፈጅቶባታል። ለጉዞዋም 35 000 እንደከፈለች ትናገራለች።ገንዘቡ የተገኘው የገዛችውን መሬት ሸጣ ነው። ቤተሰቦቿ ዳግም እንዳትሰደድ ከልክለዋት ነበር።ወጣቷም በህገወጥ መንገድ ባህር አቋርጣ ስትመጣ ሞት ድረስ አደጋ ሊደርስባት እንደሚችል ታውቅ ነበር።

ሞገስ በበኩሉ በጠቅላላው ኢትዮጵያ አራት ወር ከቆየ በኋላ ነው ተመልሶ ወደ ሳውዳ አረቢያ ጉዞ የጀመረው። በአሁኑ ሰዓት የበግ ዕረኛ ነው።

ኤልሳና ሞገስ ተመልሰው ከሀገር ቢወጡም ሌሎችን የሚመክሩት በኢትዮጵያ መቆየቱን ነው። ከሳውዲ አረቢያ የተባረሩት የኢትዮጵያ ስደተኞች በጋራ ተደራጅተው የሚሰሩበት ሁኔታ ስለመፈጠሩ እና ስራው ምን እንደሚመስል ፤ ከሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። ነገር ግን ለስራ ከሳውዲ ተመላሾች የሚገኙነት አካባቢ ተጉዘው ሳሉ በስልክ ያገኘናቸው ወይዘሮ አይዳ አወል የሚከተለውን ብለውናል። ወይዘሮ አይዳ በአለም ዓቀፍ ስራ ድርጅት በምህፃሩ ILO የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የቴክኒክ ክፍል ዋና አማካሪ ናቸው።

ዝርዝሩን ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል፤

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic