ወደ ማሳ የቀረቡት የግብርና ውጤቶች ማቀነባበሪያዎች | ኢትዮጵያ | DW | 06.02.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ወደ ማሳ የቀረቡት የግብርና ውጤቶች ማቀነባበሪያዎች

ከአቮካዶ ዘይት የሚያመርት የኔዘርላንድስ ኩባንያ በይርጋለም የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ሥራ ለመጀመር ዝግጅት ላይ ነው። የይርጋለም የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ በኢትዮጵያ ከሚገነቡ አራት መሰል ተቋማት አንዱ ነው። ወደ ገበሬው ማሳ የቀረቡት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ለኢትዮጵያ ግብርና እና ለምጣኔ-ሐብቱ ምን ይፈይዱ ይሆን?

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:26

በትግራይ፤አማራ፤ደቡብና ኦሮሚያ አራት ፓርኮች በግንባታ ላይ ናቸው

የይርጋለም የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ የኢንዱስትሪ ፓርክ በመጪዎቹ ሁለት ወራት የመጀመሪያ ምርቶች ይፋ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል። የደቡብ ክልል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ብሩ ወልዴ ለDW እንደ ተናገሩት የአቮካዶ እና የማር አቀነባባሪዎች የሚጠቀሙባቸው መጠለያዎች ተጠናቀዋል። በሥራው ለመሰማራት የፈለጉ ኩባንያዎችም ማሽኖችን ከቦታው አድርሰዋል።

አቶ ብሩ "ከሁለት ወር በኋላ የዘይት ምርት ይጀመራል ብለን እንጠብቃለን። ለዚህ ቅድመ-ዝግጅት ቀን ከለሊት እየሰራን እንገኛለን። ካምፓኒዎችም ማሽነሪዎች አምጥተው ግንባታው በሚካሔድበት ቦታ አስቀምጠዋል" ሲሉ ተናግረዋል። 

አቶ ብሩ እንደሚሉት የማሰልጠኛ እና የገበያ ማዕከል ግንባታዎች ተካሒዷል። የፓርኩ የአስተዳደር ሕንጻ ግንባታም ተጠናቋል። የውሐ እና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦቶች ተሟልተውለታል። የመንገድ ግንባታው በመካሔድ ላይ ነው።  

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ

እሸቴ በቀለ

ኂሩት መለሰ 

Audios and videos on the topic