ወይዘሪት ብርቱኳን | ኢትዮጵያ | DW | 11.05.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ወይዘሪት ብርቱኳን

ከዛሬ ሶሶት ወር አንስቶ በዕስር ላይ ለሚገኙት ለአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ለወይዘሪት ብርቱኳን ሚዴቅሳ በለንደን ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ትናንት ለንደን ውስጥ የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት ተካሂዷል ።

default

አስተባባሪዎች እንዳሉት የሻማ ማእብራት የስ ነስርዓቱ ዓላማ የሚታወቅ ሀቅ ክደው በማስፈራሪያ ተረትተው የዘላለም የህሊና ዕስረኛ ከመሆን የመጣውን ሁሉ ለመቀበል ወስነው እዕስር ለተዳረጉት ለወይዘሪት ብርቱኳን ሚዴቅሳ ያላቸውን አክብሮት ማሳየትና የትግል አጋርነታቸውን መግለፅ ነው ። በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኘችው የለንደንዋ ዘጋቢያችን ሀና ደምሴ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች ።

ሀና ደምሴ/ ሂሩት መለሰ /አርያም ተክሌ