ወባ ዛሬም ታሳስባለች | ጤና እና አካባቢ | DW | 27.04.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

ወባ ዛሬም ታሳስባለች

ወባን ለመከላከል የሚረዳ ክትባት ለማምረት ጥረት እየተደረገ ነዉ።

default

በዓለም ባንክና የማይክሮ ሶፍት ተባባሪ መስራች ቢል ጌት በገንዘብ የሚደግፉት ዋነኛዉ የዓለም የጤና ተቋም መቶ በመቶ በተባለለት ደረጃ ዉጤታማ የሆነ የወባ መከላከያ ክትባት እየተዘጋጀ እንደሆነ ትናንት የዓለም የወባ ቀን ሲታሰብ የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። ወባ በተለይ በአፍሪቃ ዋነኛዉ የጤና ስጋት ከመሆን አልፎ ለበርካቶች ህይወት ማለፍ ምክንያት መሆኑ ይነገራል። አሁን በየአካባቢዉ ተጠናክረዉ የሚከናወኑት የወባ በሽታን መስፋፋት የመግቻ ስልቶች በዚሁ ከቀጠሉ እንደባለሙያዎች እምነት በመጪዉ የአዉሮጳዉያን 2015ዓ,ም በወባ ምክንያት የሰዉ ህይወት መቀጠፉ ያከትምለታል።

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ