ወባን የማጥፋት ጥረት | ጤና እና አካባቢ | DW | 27.04.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

ወባን የማጥፋት ጥረት

በዓለማችን ለበርካታ ሰዎች ህይወት መቀጠፍ ምክንያት ከሆኑ የጤና ችግሮች ወባ አንዱ ነዉ። እንዲያም ሆኖ ወባ መከላከል ሲቻል ሞት የሚያስከትል በሽታ መሆኑ የጤና ባለሙያዎቹን ያስማማል።

default

...አጎበር፤ የወባ ትንኝ ደህና ሰንብች...

የዘንድሮዉን የወባ ቀን ምክንያት በማድረግ የተመ የህፃናት መርጃ ድርጅት UNICEF ይፋ ባደረገዉ መሰረት በዓለም ዙሪያ በወባ ምክንያት በየዓመቱ የ850,000 ሰዎች ህይወት እንደዋዛ ይቀጠፋል። በተለይ ይህ ጉዳት በአፍሪቃ ከሰሐራ በስተደቡብ በሚገኙ አገራት ይጠናል። ከተጠቀሰዉ ቁጥር ዘጠና በመቶዉ የሚከሰተዉ በዚሁ አካባቢ ነዉና። በኢትዮጵያ በድሬደዋና በጉራጌ ዞን አካባቢ ወባን መቆጣጠር ብሎም ለማጥፋት ከፍተኛ ተግባር ተከናዉኗል። ድሬደዋ ወባን ታሪክ አድርጌያለሁ ትላለች።

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ