የወልቃይት ጠገዴ እና የራያ ዉዝግብ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 18 2011ማስታወቂያ
በትግራይ መስተዳድር ሥር የሚገኙት የወልቃይት ጠገዴ እና የራያ ግዛቶች ወደ አማራ መስተዳድር እንዲመለሱ ተቃዋሚዉ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) መሪዎች ጠየቁ።ሰሞኑን በአራት የአዉሮጳ ሐገራት ለሚኖሩ የአማራ ተወላጆች የፓርቲያቸዉን ዓላማ ያስተዋወቁት የአብን መሪዎች በአማራ ሕዝብ ላይ ተፈፅሟል ላሉት ግፍ ካሳ እንዲከፈል ጠይቀዋልም።ባለሥልጣናቱ በአዉሮጳ ለሁለት ሳምንት ያደረጉትን ጉብኝት ባለፈዉ ዕሁድ ፓሪስ-ፈረንሳይ ዉስጥ ባደረጉት ስብሰባ አጠናቅቀዋል።የፓሪሷ ወኪላችን ባለሥልጣናቱን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ ልካልናለች።
ኃይማኖት ጥሩነህ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ