ኮንጎና የተመድ ባለሥልጣናት ጉብኝት | አፍሪቃ | DW | 08.10.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ኮንጎና የተመድ ባለሥልጣናት ጉብኝት

ግዛቲቱን የሚያወድመዉ ጦርነት ለወትሮዉ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ማዕከላዊ መንግሥት እና በሩዋንዳና በዩጋንዳ ይታገዛሉ የሚባሉት የM23 አማፂያን ነበር።ከቅርብ ጊዜ ወዲሕ ግን የኮንጎ መንግሥት ጦር፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጦር፥ በዉጤቱም ጦር ያዋጡት መንግሥታት እና የአማፂያን እና የአማፂያኑ ደጋፊዎች ዉጊያ ሆኗል።

©Kyodo/MAXPPP - 11/12/2012 ; GOMA, Democratic Republic of Congo - Soldiers of the M23 rebel movement hold weapons aboard a vehicle in Sake near Goma, the Democratic Republic of the Congo, on Nov. 30, 2012. (Photo by Takeshi Kuno) (Kyodo)

የ M23 ተዋጊዎች


የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት አባል ሐገራት አምባሳዳሮች በኮንጎ እና በሩዋንዳ የሚያደርጉትን ጉብኝት አጠናቀዉ አዲስ አበባ ገብተዋል።አስራ-አምስቱ የምክር ቤቱ አምባሳደሮች ኪንሻሳና፥ ጎማ ከኮንጎ መንግሥት ባለሥልጣናት እና ኮንጎ ከሠፈረዉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጦር፥ አዛዦች ጋር ተወያይተዋል።በጦርነቱ የተፈናቀሉ ነዋሪዎችንም አነጋግረዋል።የዶቸ ቬለዉ ጋዩዉስ ኮዋኔ እንደዘገበዉ አምባሳደሮቹ ከጦር አዛዦቹና ከባለሥልጣናቱ ጋር ያደረጉት ዉይይት «ጣልቃ ገብ ብርጌድ» በተሰኘዉ በዓለም አቀፉ ጦር ተልዕኮ ላይ ያተኮረ ነበር።ነጋሽ መሐመድ ዝር ዝሩን አጠናቅሮታል።

አምባሳደሮቹ ከኒዮርክ-ኪንሻ፥ ከኪንሻ-ጎማ፥ ከጎማ-ኪጋሊ ብለዉ ዛሬን አዲስ አበባ ነዉ የዋሉት። በኪንሻ ቆይታቸዉ ከኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ መሪዎች ጋር ላጭር ጊዜ ተነጋግረዋል።የኪንሻሳዉ ንግግር ርዕሥ፥ የጉዟቸዉ ዓለማም አንድ ነዉ።ምሥራቃዊ ኮንጎና ጦርነቷ።ወዲያዉ ጦርነቱ ወደ ሚያወድማት ወደ ምሥራቃዊ ኮንጎ፥ «ሰሜናዊ ኪቩ» ግዛት ዋና ከተማ ዘለቁ።ጎማ።

Democratic Republic of Congo (FARDC) soldiers celebrate near Kibati, near Goma on September 4, 2013. M23 army mutineers, whose 16-month rebellion had seen them occupying Kibati for over a year, have retreated from their positions in the hills around Goma in the face of an offensive by the military and a new United Nations combat force. AFP PHOTO / CARL DE SOUZA (Photo credit should read CARL DE SOUZA/AFP/Getty Images)

የመንግሥት ጦርግዛቲቱን የሚያወድመዉ ጦርነት ለወትሮዉ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ማዕከላዊ መንግሥት እና በሩዋንዳና በዩጋንዳ ይታገዛሉ የሚባሉት የM23 አማፂያን ነበር።ከቅርብ ጊዜ ወዲሕ ግን የኮንጎ መንግሥት ጦር፥ ከመንግሥት ጦር የወገነዉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጦር፥ በዉጤቱም ጦር ያዋጡት መንግሥታት እና የአማፂያን እና የአማፂያኑ ደጋፊዎች ዉጊያ ሆኗል።

ግዙፉን የዓለም ማሕበር የሚወክሉት አሥራ-አምስቱ አምባሳደሮች ኪንሻም፥ ጎማም ያደረጉት ዉይይትም አብዛኛዉ ዓለም ባንድ ጎራ በቆመበት ዉጊያ የሚያሸንፍበትን ጥቅል ሥልት ከማብሰልሰል ያለፈ አይደለም።እንግረ-መንገዳቸዉንም ጦርነቱ ያፈናቀላቸዉ ሰዎች ከተጠለሉበት መንደር ቢያንስ አንዱን መጎብኘታቸዉ፥ የተፈናቃዮቹን የሰሥቃይ-ሰቆቃ መስማታቸዉ በጨረፍታም ቢሆን መስማታቸዉ አልቀረም።

«ከሁሉም ሥፍራ የሚመጡ ነጮችን ሥንቀበል ኖረናል።እናንተ ግን ለኛ ሠላም የማምጣት ሥልጣን አላቸሁ ማለትን ሰማን።ባሎቻችን ሞተዋል።ልጆቻችን ተገድለዋል።እሕል ዉሐ ፍለጋ ከተንቀሳቀስን እንደፈራለን።አንዳዶቻችን በኤች አይ ቪና በሌሎች በወሲብ በሚተላለፉ በሽታዎች ተለክፈናል።»

አሉ አንዷ።ሌሎቹ አለቀሱ።የተቀሩት ተማፅኗቸዉን አወረዱት።

«እባካችሁ ሠላም እንዲወርድ እርዱን፥ ርዳታችሁን እንለምናለን፥ እንማፀናለን። ሠላም ሥጡን፥ ሠላም እንፈልጋለን።» እያሉ።

ለዋይታ-ለቅሶ ተማፅኖዉ፥ የወቅቱ የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ፕሬዝዳትና የጎብኚዎቹ መሪ አምባሳደር ጌሪይ ኩዊንላን መልስ ሰጡ።

«የጉብኝታችን ዓላማ በካምፓላዉ የሰላም ሒደትና በአዲስ አበባዉ የመግባቢያ ዉል መሠረት የተገባዉ ቃል ገቢራዊነትን በአካል ለማረጋገጥ ነዉ።አሁንም ቢሆን ብዙ መሠራት ያለባቸዉ ነገሮች አሉ።ይሑንና ኮንጎ በተገቢዉ ጎዳና እየተጓዘች ነዉ።ሁላችሁም ፍላጎታችሁ እንዲሳካላችሁ እንመኛለን።»

A child stands in front of Indian soldiers of the UN mission in the Democratic Republic of Congo (MONUSCO) driving an armoured vehicle at the border zone in Kagnaruchinya, 7 km north of Goma, on June 2, 2013. The M23 rebellion -- launched by Tutsi former soldiers who mutinied in April 2012 -- is the latest in years of violence that have ravaged the vast central African country's mineral-rich east. A peace deal signed in February by 11 regional countries had brought relative calm until it was broken in the three days leading up to Ban's visit. The two sides stopped fighting while the UN leader toured the flashpoint city of Goma. AFP PHOTO/Junior D. Kannah (Photo credit should read Junior D. Kannah/AFP/Getty Images) Erstellt am: 02 Jun 2013

የተመድ ጦር

ምሥራቃዊ ኮንጎ ከሚኖረዉ ከየሥድስቱ ሰዉ አንዱ ተፈናቃይ ነዉ።የመንግሥት ጦርም፥ አማፂያንም፥ተራ ሽፍቶችም ወንዱን ይገድላሉ፥ አለያም ለዉጊያ ያዘምታሉ።ሴቱን ይደፍራሉ። አምባሳደሮቹ ኪንሻሳን ሲጎበኙ የኮንጎ መንግሥት ቢያንስ አንድ መቶ ሰላሳ ሴቶችን አስገድደዉ መድፈራቸዉ የተመሠከረባቸዉን ወታደሮቹን ለፍርድ እንዲያቀርብ ዩናይትድ ስቴትስና ብሪታንያ መጠየቃቸዉ ተዘግቧል።

አምባሳደሮቹ ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ ከአፍሪቃ ሕብረት ባለሥልጣናት ጋር ያደረጉት ዉይይት ዋና ርዕሥም የኮንጎ ጦርነት ነዉ።

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠAudios and videos on the topic