ኮሮና በአውሮጳ ያሳደረው ተጽእኖ  | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 24.03.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

ኮሮና በአውሮጳ ያሳደረው ተጽእኖ 

በአሜሪካ እና በአውሮጳ ተህዋሲው በአስደንጋጭ ፍጥነት እየተሰራጨ ነው።የዓለም የጤና ድርጅት ትናንት ማምሻውን ባወጣው ዘገባ በአውሮጳ ተህዋሲው የያዛቸው ቁጥር በ24 ሰዓታት ውስጥ በ20,131 ከፍ ብሏል።እስከ ትናንት ድረስ በአውሮጳ ተህዋሲው የተገኘባቸው ቁጥር 171 424  መሆኑ ሲገለጽ የሞቱት ቁጥር ደግሞ ከ8 ሺህ በልጧል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 06:56

ኮሮና በአውሮጳ

በዓለማችን በኮሮና ተህዋሲ የሚያዘው ሰው ቁጥር ማሻቀቡ ቀጥሏል። የሚሞተውም እንዲሁ።እስካሁን በዓለማችን ከ386 ሺህ በላይ ሰዎችን የያዘው ኮሮና ቁጥሩ 17 ሺህ የሚጠጋውን ገድሏል።በተለይ በአሜሪካ እና በአውሮጳ ተህዋሲው በአስደንጋጭ ፍጥነት እየተሰራጨ ነው።የዓለም የጤና ድርጅት ትናንት ማምሻውን ባወጣው ዘገባ በአውሮጳ ተህዋሲው የያዛቸው ቁጥር በ24 ሰዓታት ውስጥ በ20,131 ከፍ ብሏል።እስከ ትናንት ድረስ በአውሮጳ ተህዋሲው የተገኘባቸው ቁጥር 171 424  መሆኑ ሲገለጽ የሞቱት ቁጥር ደግሞ ከ8 ሺህ በልጧል።በዩናይትድ

ስቴትስ  በኮሮና 31 573 ሰዎች ሲያዙ ከ400 በላይ ሰዎች በተህዋሲው ህይወታቸው አልፏል።የአውሮጳ መንግሥታት ሥርጭቱን ለመቀነስ ከአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አንስቶ ልዩ ልዩ ክልከላዎችን ተግባራዊ ቢያደርጉም የተህዋሲው ሥርጭት ፍጥነት መቀነስ አላሳየም። ኮሮና በአውሮጳ ያሳደረው ተጽእኖ የዛሬው አውሮጳ እና ጀርመን ትኩረት ነው።

ገበያው ንጉሴ  

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic