ክፍል 50 - ጀርመንኛ እንደ የውጭ ቋንቋ | Radio D Teil 2 | DW | 10.11.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

Radio D Teil 2

ክፍል 50 - ጀርመንኛ እንደ የውጭ ቋንቋ

ያን ልዩ የጀርመንኛ ፕሮጀክት የሚሰጥበት አንድ ትምህርት ቤት ይጎበኛል። ያን ተማሪዎች አፍ ከፈቱበት ቋንቋ ጎን ለምን ጀርመንኛ ቋንቋን መማር እንደፈለጉ እና ስለ ወደፊት አላማቸው ይጠይቃቸዋል።

ያን 80 ከመቶ የሚሆኑ የውጭ ሀገር ዜጎች ወደሚማሩበት ትምህርት ቤት በመሄድ አንድ ልዩ የጀርመንኛ ፕሮጀክት ያቀርባል። በትምህርት ቤቱ ከቭላድሚር፣የን-ሊን እና ጉልሰርን ጋር ይተዋወቃል። ተማሪዎቹ ስለ ሁለቱ የተለያዩ ቋንቋዎች ያላቸውን ተሞክሮ እና ጀርመንኛ ቋንቋ ትምህርት ላይ ምን እንደሚከብዳቸው ያጫውቱታል።
ፕሮፌሰሩ ዛሬ ተማሪዎቻቸውን ከአዲስ የሰዋሰው ትምህርት ነፃ አድርገዋቸዋል። የኃላፊ ጊዜን የሚያመላክት ዓረፍተ ነገር ውስጥ "bevor" የሚለውን ቃል አገባብ ብቻ ያብራራሉ።

Downloads