ክፍል 48 - ምስራቅ እና ምዕራብ | Radio D Teil 2 | DW | 10.11.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

Radio D Teil 2

ክፍል 48 - ምስራቅ እና ምዕራብ

በ Radio D ስቱዲዮ ፓውላ ለዛሬ ስለ ጀርመን ውህደት ትመለከታለች። ስለዚሁ ጉዳይ የሚወያዩ የተወሰኑ እንግዶች ወደ ስቱዲዮ ጋብዛለች።

ፓውላ የምትመራው ውይይት ርዕስ« ምስራቅ እና ምዕራብ ጀርመናውያን» ይሰኛል። ውይይቱን ከአንድ ምስራቅ ጀርመናዊ የመኪና መካኒክ ፣ አንድ የስነ-ዓዕምሮ ባለሙያ እና ከአንድ የኢኮኖሚ ምሁር ጋር ነው የምታካሂደው። ለእንግዶቿ ከምታቀርባቸው ጥያቄዎች መካከል አሁን ድረስ ምክንያት የለሽ አሉታዊ አስተሳሰብ አለ? ወደፊት ምስራቅ እና ምዕራብ ጀርመናውያን ጥሩ ግንኙነት እንዲኖራቸው መፍትሄው ምንድን ነው? የሚሉ ይገኙባቸዋል።
ፕሮፌሰሩም ቢሆኑ ከባድ ጥያቄ ይጠብቃቸዋል። "haben" እና "sein" የሚሉትን ቃላት “würde” ከሚለው ቃል ጋር እንዴት እንደሚገባ ያብራራሉ።

Downloads