ክፍል 47 - የግንብ ግንባታ | Radio D Teil 2 | DW | 10.11.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

Radio D Teil 2

ክፍል 47 - የግንብ ግንባታ

ፓውላ፣ ፊሊፕ፣ ያን እና ዮሰፊን በርሊንን በመኪና ሲዞሩ በራይሽስታግ፣ ብራንድንቡርገር በር እና የፈረሰው የጀርመን ግንብ የቆመበትን መስመር የሚጠቁመው መንገድ ያልፋሉ። Radio D ግንቡ እንዴት እንደተገነባ የሚገልፅ ዘገባ አለው።

እኢአ ነሀሴ 13 ቀን 1961 ዓ,ም ምሽት የቀድሞዋ ምስራቅ ጀርመን ፖሊስ ከምዕራብ ጀርመን ጋር የሚያዋስነውን ድንበር በግንብ ማጠር ይጀምራል። ቤታቸው ልክ ድንበሩ ላይ የነበሩ ጥንዶች በፍጥነት ለመሰደድ ይወስናሉ። በምዕራብ ጀርመን በኩል ከፎቅ የሚዘሉትን ሰዎች ለማትረፍ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ይሯሯጣሉ።
በዛሬው የሰዋሰው ትምህርት "ein" የሚለው ያልተወሰነ ደቂቅ ቅጽል እና "eins" የሚለውን ተውላጠ ስም ተቀምጠዋል። ፕሮፌሰሩ በዚህ አገባብ ላይ ወሳኝ ስለሆኑት ደንቦች ያብራራሉ።

Downloads