ክፍል 46 - የበርሊን ድቦች | Radio D Teil 2 | DW | 10.11.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

Radio D Teil 2

ክፍል 46 - የበርሊን ድቦች

ፓውላ እና ፊሊፕ በርሊን ውስጥ "United Buddy Bears" በሚል አንድ የስዕል ፕሮጀክት ይጎበኛሉ። በዚህ ዝግጅት ከ 120 ሀገራት የተውጣጡ ሰዓሊዎች ተካፍለውበታል። አንድ ቃለ መጠይቅ ደግሞ ስለዚህ ፕሮጀክት የበለጠ ለመረዳት ይረዳል።

ፓውላ እና ፊሊፕ ወደ በርሊን ተመልሰው ከዮሰፊን እና ያን ጋር በዋና ከተማዋ ይንሸራሸራሉ። በተለይ ዮሰፊን በአንድ የጥበብ ስራ ይበልጥ ተስባለች። 120 ትላልቅ ከፕላስቲክ የተሰሩ ድቦች የመቻቻል ምልዕክት ሆነው ተቀምጠዋል። ጋዜጠኞቹ የድርጅቱን ቃል አቀባይ በመጠየቅ በተለያዩ ቀለማት ስላሸበረቁት ድቦች የበለጠ ይረዳሉ። ሌሎቹ በበርሊን ከተማ ሲንሸራሸሩ ፕሮፌሰሩ በስራ ተጠምደዋል። ከአንድ ባለቤት ፊትለፊት የሚገቡ ቅፅሎችን ማለቂያ ያስረዳሉ። ቀላል ስራ አይደለም።

Downloads