ክፍል 44- የትላልቅ ምሁሮች ከተማ | Radio D Teil 2 | DW | 10.11.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

Radio D Teil 2

ክፍል 44- የትላልቅ ምሁሮች ከተማ

በ18ኛው ክፍለ ዘመን የና በርካታ ምሁሮችን ወደ ከተማዋ ትስብ ነበር። ከነዚህ መካከል አንዱ ፍሪድሪሽ ሺለር ነበሩ። ፊሊፕ እና ፓውላ ምሁሩ የና ከተማ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰጡትን ትምህርት ያሰሙናል።

በዚህ ክፍል አድማጮች የበለጠ ስለ ሺለር እና ጎይተ እየተረዱ የና ከተማ በ18ኛው ክፍለ ዘመን ስለነበረው ይረዳሉ። ሺለር በ29 ዓመታቸው ነበር በከፍተኛ ተቋም ለመጀመሪያ ጊዜ ማስተማር የጀመሩት። የዛን ዕለት ከ 500 በላይ ተማሪዎች ተገኝተዋል። በወቅቱ የተገኘውም ሰው ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ስለነበር አዲስ ቦታ መፈለግ ግድ ብሏል። ፕሮፌሰሩ አድማጭን ከጥንት ጊዜ መልሰው ወደፊት የሚሆነውን ይነግራሉ።ለዚህም "werden" የሚለውን ግሥ ይጠቀማሉ።

Downloads