ክፍል 35- ቤትሆፈን ቤትሆፈንን ይጫወታል | Radio D Teil 2 | DW | 09.11.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

Radio D Teil 2

ክፍል 35- ቤትሆፈን ቤትሆፈንን ይጫወታል

ሁለቱ የ Radio D ጋዜጠኞች የሙዚቃ ተማሪዎቹ ግምት ትክክል ይሆን ሲሉ ይጠይቃሉ። ነገር ግን ኡላሊያ አንድ ርምጃ ቀድማቸዋለች። እሷም ሌሊቱን የደረሰችበት አንድ ነገር አለ።

በድንገት ቦን ከተፍ ያለችው ኡላሊያ ፊሊፕ እና ፓውላን እንደገና ትረዳለች። ማንነቱ ያልታወቀውን የፒያኖ ተጫዋች እሷ አስቀድማ አይታዋለች፣ ሙዚቃውም ከየት እንደመጣ ታውቃለች። የ Radio D ጋዜጠኞችም የጉጉቷን ኡላሊያ ምክር ተከትለው ከ «ወጣቱ ቤትሆፈንን» ጋር ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ፈልገዋል። ሙዚቀኛውን ለማግኘት ይሳካላቸው ይሆን?
ፓውላ እና ፊሊፕ ግራ የአስገራሚውን የፒያኖ ተጫዋች ምስጢር ገና ባይደርሱበትም፣ የኛ ፕሮፌሰር ግን ጥገኛ ሀረግን በመጠቀም እንዴት ምክንያት ማቅረብ እንደሚቻል ያብራራሉ።

Downloads