ክፍል 33- አዲስ ባልደረባ | Radio D Teil 2 | DW | 09.11.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

Radio D Teil 2

ክፍል 33- አዲስ ባልደረባ

ያን በ Radio D ተለማማጅ ሆኖ መስራት የጀመረበት ቀን ነው። ፓውላ እና ፊሊፕ ግን እሱን ለመርዳት ምንም ጊዜ የላቸውም። ምክንያቱም ኮምፑ ለሁለቱ ጋዜጠኞች አዲስ ስራ አዘጋጅቶላቸዋል። ጋዜጠኞቹ በፍጥነት ወደ ቦን መሄድ አለባቸው።

ያን የመገናኛ ብዙኃኑን ባልደረቦች በሙሉ ተዋውቆ እንደጨረሰ ስለ አንድ ርዕስ መረጃ የማሰባሰብ ስራ ይሰጠዋል። ፓውላ እና ፊሊፕ ደግሞ እውቁ የሙዚቃ አቀናባሪ ቤትሆፈን የትውልድ ስፍራ በሆነችው ቦን ከተማ ሌሊት ያልታሰቡ ነገሮች በመከሰታቸው በፍጥነት ወደ ቦን ከተማ መጓዝ ነበረባቸው። እነሱም በቦታው በመገኘት ጉዳዩን የማጣራት ስራቸውን ወዲያው ይጀምራሉ።
ፕሮፌሰሩ በዚሁ ጊዜ ቤትሆፈን ቤት ከተከሰተው ነገር ይልቅ ብዙም ግራ የማያጋባውን ቀጥተኛ ያልሆኑ ጥያቄያዊ ዓረፍተ ነገሮች አሰካክን በደንብ ያብራራሉ።

Downloads