ክፍል 31- አንድ ፣ሁለት፣ ሶስት! | Radio D Teil 2 | DW | 09.11.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

Radio D Teil 2

ክፍል 31- አንድ ፣ሁለት፣ ሶስት!

ግሩንሀይደ ውስጥ እንግዳ የሆኑ ነገሮች እየተከሰቱ ነው። ትራቢው እንዴት ብሎ ነው ፈጣኑን መኪና ፖርሼ ሊቀድም የቻለው? ከፓውላ ጋር ወደ ሞልንዜ የተጓዘው ብልሁ ያን ሚስጥሩ ምን እንደሆነ ያውቃል።

ፓውላ በሞልንዜ ጉዞዋ ወቅት ዕድሜ ከያን ቤከር ጋር አንድ አስገራሚ ግኝት ታደርጋለች። እሽቅድድሙን በተመለከተ አንድ ልክ ያልሆነ ነገር ያለ ይመስላል። ፓውላ የትራቢውን ሹፌር የተጠቀመበትን የማጭበርበር ዘዴ ትደርስበታለች። ፊሊፕስ ስለዚህ ምን ያውቅ ይሆን? ፊሊፕ በትራቢው ሹፌር ጉንተር የተታለለ ይመስላል።
ይህ ሁኔታ ፕሮፌሰሩን ብዙም ግራ አላጋባም። በዚህ አጋጣሚ የተለያዩ የኃላፊ ጊዜ ግሶችን ህጎችን ያብራራሉ። መደበኛ ያልሆኑ ግሶችን "haben" እና "sein" ማብራራቱ እንኳን ለሳቸው ችግር አይደሉም።

Downloads