ክፍል 22 – የተሰወረው የባህር ተንሳፋፊ | Radio D Teil 1 | DW | 22.09.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

Radio D Teil 1

ክፍል 22 – የተሰወረው የባህር ተንሳፋፊ

ፊሊፕና ፓውላ ስለ አካባቢው አንድ ፍንጭ ለማግኘት ጉዞ ይጀምራል። እነሱም አዳዲስ የሚገርሙ ግኝቶች ያደርጋሉ፦ ሰርፈረኛ የሌለበት የሰርፍ ጣውላ እና ግራ የሚያጋባ የጋዜጣ ፁሁፍ ትኩረታቸውን ያጠናክረዋል።

ከስፍራው ትንሽ ራቅ ብሎ ሁለት ጋዜጠኞች ስለ አስገራሚው አሳ ነባሪ ያፈላልጋሉ። አንድ የባህር ተንሳፋፊ የሌለበት የሰርፍ ጣውላ ክፉ ነገር ሳይከሰት እንዳልቀረ ያመለክታል። በኋላም የሀምቡርግ ጋዜጣ ላይ የተባለውን አሳ ነባሪና የፊሊፕና የላውራን ፎቶ ያገኛሉ። ሁለቱም በፍርሀት ይመለከቱ ነበር። ግን ይሄ ሁላ እንዴት አንድ ላይ ትርጉም ሊሰጥ ይችላል?

ቢያንስ ሰዋሰውን ስንመለከት ትርጉም የሚሰጡ ነገሮች አሉ። ይህ ምዕራፍ የበለጠ ትኩረት የሚሰጠው "sie" እና "er" ለሚሉት ተወላጠ ስሞች ነው። ከዚህ በፊት በነበረው ክፍል የተመለከትናቸውን አርቲክሎች ከዋናው ቃል ጋር መዛመድ ያስፈልጋል።

Downloads