ክላዉስ ቮቨራይት ለሶስተኛ ግዜ በርሊንን ያስተዳድራሉ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 19.09.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ክላዉስ ቮቨራይት ለሶስተኛ ግዜ በርሊንን ያስተዳድራሉ

ከ16ቱ የጀርመን ግዛቶች ዋነኛ በሆነዉ በበርሊን ግዛት ትናንት በተካሄደዉ የአካባቢ ምርጫ የሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ 28,3 በመቶ የመራጭ ድምጽን በማግኘት አሸናፊ ሆንዋል።

default

ከ16ቱ የጀርመን ግዛቶች ዋነኛ በሆነዉ በበርሊን ግዛት ትናንት በተካሄደዉ የአካባቢ ምርጫ የሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ 28,3 በመቶ የመራጭ ድምጽን በማግኘት አሸናፊ ሆንዋል። መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የሚገኙበት የክርስትያን ዴሞክራቲክ ህብረት ፓርቲ 23,4 በመቶ፣ አረንጓዴዎች 17,6 በመቶ፣ እንዲሁም ግራ አዘንባዪ ፓርቲ 11,7 በመቶ የመራጭን ድምጽ በማግኘት ዉጤቱ ተጠናቆዋል። በምርጫዉ ዉጤት መሰረት አሁንም የሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲዉ ክላዉስ ቮቨራይት በስልጣን ይቆያሉ። የጀርመን መንግስት ተጣማሪ የሆነዉ የነጻ ዲሞክራቶች ፓርቲ FDP በዚህ ምርጫ ለሶስተኛ ግዜ ከባድ ሽንፈት ደርሶበታል። በዚህም በበርሊኑ መንግስት ላይ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል ታዛቢዎች ያምናሉ። ከጎርጎረሳዉያኑ 2002 አ.ም ጀምሮ ከሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ ጋር ተጣምሮ በርሊንን ሲያስተዳድር የቆየዉ የግራ አዘንባዪ ፓርቲ ያለፈዉን ያህል ነጥብ ባለማግኘቱ ቦታዉን ለቆዋል። አሸናፊዎቹ SPD ማለትም የሶሻል ዲሞክራቲ ፓርቲ መንግስት ለማቆም ምናልባትም ከአረንጓዴ ፓርቲ ጋር በመደራደር የጥምረት መንግስት እንደሚፈጥሩ ነዉ የሚጠበቀዉ። በሌላ በኩል በበርሊኑ ምርጫ ላይ በጀርመንኛ Piratenpartei በቀጥታ ትርጉሙ የባህር ላይ ወንበዴዎች ፓርቲ የተሰኘዉ ቡድን 8.9 ከመቶ የመራጭ ድምጽን በማግኘት በከተማይቱ አስተዳደር ምክር ቤት ቦታን ለማግኘት መብቃቱ ህዝብን አስደምሞአል። ከዚህ ቀደም ለዚህ እድል ደርሶ የማያወቀዉ ይህ ፓርቲ ለመመረጥ የቻለዉ፣ በተለይ በኮምፒዉተር እና በመሳሰሉ ነገሮች የግለሰቦች ሰነድን እንዲጠበቅ ባደረገዉ ብርቱ ቅስቀሳ ነዉ።

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ