ኬንያ ግዙፉን የስደተኞች መጠለያ ልትዘጋ ነዉ | አፍሪቃ | DW | 12.04.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ኬንያ ግዙፉን የስደተኞች መጠለያ ልትዘጋ ነዉ

በሶማልያ የሚንቀሳቀሰዉ ነዉጠኛ ቡድን አሸባብ ባለፈዉ ሳምንት በኬንያ ጋሪሳ ዩንቨርስቲ ኮሌጅ 150 ሰዎችን ከገደለ በኋላ የኬንያ መንግሥት ዳዳብ የስደተኞች መጠለያ ጣብያን እንደሚዘጋ አስታወቀ።

የኬንያ ምክትል ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ዛሬ እንዳስታወቁት «የተመ የስደተኞች ጉዳይ መሥርያ ቤት 350 ሺህ ስደተኞችን የያዘዉ የዳዳብ መጠለያ ጣብያን በሶስት ወር ግዜ ዉስጥ ወደ ሶማልያ መዛወር ይኖርበታል። የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ መሥርያ ቤት ይህን ጥያቄ ካላሟላ ኬንያ ራስዋ ስደተኞችን ወደ ሶማልያ ታዛዉራለች ሲሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ሩቶ አስጠንቅቀዋል።

ከተቋቋመ ከ 20 ዓመት በላይ የሆነዉ የዳዳብ የስደተኞች መጠለያ ጣብያ ፤ በአብዛኛዉ ከጎረቤት ሶማልያ በአሸባብ ጥቃት

Explosion an der Universität von Nairobi

ጉዳት የደረሰበት ተማሪ

ከቤት ንብረታቸዉ የተፈናቀሉ ሶማልያዉያን ስደተኞች መኖርያ መሆኑ ይታወቃል። ከኧልቃይዳ ጋር ግንኙነት እንዳለዉ የሚነገረዉ ነዉጠኛዉ የአሸባብ ቡድን በኬንያ ተደጋጋሚ ጥቃትን ማድረሱ ይታወቃል። የአሸባብ እንቅስቃሴን ለመግታት የናይሮቢዉ መንግሥት ወደ 5000 ጦር ሰራዊቱን በሶማልያ ማሰማራቱም ይታወቃል።

በሌላ ዜና ኬንያ ናይሮቢ በሚገኝ ዩንቨርስቲ የተማሪዎች መኖርያ ላይ በደረሰ የኤሌትሪክ ፍንዳታ ፤ አንድ ሰዉ ሞተ ሌሎች ወደ 150 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደረሰባቸዉ። ተማሪዎቹ ጉዳት የደረሰባቸው አዲስ የሽብር ጥቃት የተጣለ በስሏቸው ከ5ኛው ፎቅ ለመሸሽ ባደረጉት ሙከራ እንደሆነ ተያይዞ ተዘቅሷል።

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ