ኬንያ የጥላቻ ንግግር | አፍሪቃ | DW | 15.06.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ኬንያ የጥላቻ ንግግር

በኬንያ ሕገ-መንግሥት መሠረት ዘርና ጎሳን የሚያጥላላ ንግግር ማድረግ ከባድ ቅጣት የሚያስጥል ወንጀል ነዉ። በመጪዉ የጎርጎሪያኑ 2017 አጋማሽ በሚደረገዉ ምርጫ የሚወዳደሩ ፖለቲከኞችና ደጋፊዎቻቸዉ ግን አልፎ አልፎ ሕገ-መንግሥቱን እየጣሱ እንዳቸዉ የሌላዉን ጎሳ ወይም ዘር የሚያጥላላ ንግግር ያሰማሉ

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:17

ኬንያ የጥላቻ ንግግር

የኬንያ ፖሊስ በጎሳና የጥላቻ ንግግር አድርገዋል ያለቸዉን ሥምንት የምክር ቤት እንደራሴዎችን አሠረ።ፖሊስ እንደሚለዉ ሰወስት የገዢዉ ፓርቲ እና አምስት የተቃዋሚ ፓርቲ እንደራሴዎች በየፊናቸዉ በጠሩት የምርጫ ዘመቻ፤ አንዳቸዉ የሌላቸዉን ጎሳ የሚያጥላላ ንግግር ለማድረጋቸዉ በቪዲዮ የተደገፈ መረጃ አለዉ።የሐገሪቱ ፍርድ ቤትም በተጠርጣሪዎቹ ላይ ፖሊስ የሚያደርገዉን ምርመራ እስኪያጠናቀቅ ድረስ ለአራት ተጨማሪ ቀናት እንደታየዙ እንዲቆዩ ወስኗል።በኬንያ ሕገ-መንግሥት መሠረት ዘርና ጎሳን የሚያጥላላ ንግግግር ማድረግ ከባድ ቅጣት የሚያስጥል ወንጀል ነዉ። በመጪዉ የጎርጎሪያኑ 2017 አጋማሽ በሚደረገዉ ምርጫ የሚወዳደሩ ፖለቲከኞችና ደጋፊዎቻቸዉ ግን አልፎ አልፎ ሕገ-መንግሥቱን እየጣሱ እንዳቸዉ የሌላዉን ጎሳ ወይም ዘር የሚያጥላላ ንግግር ያሰማሉ።የናይሮቢ ወኪላችንን ፋሲል ግርማን ሥለ ጉዳዩ በሥልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ፋሲል ግርማ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic