ኬንያ እና ፕሬስዋ | የጋዜጦች አምድ | DW | 03.03.2006
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የጋዜጦች አምድ

ኬንያ እና ፕሬስዋ

እክል የገጠመው የኬንያ ፕሬስ

የኬንያ ፖሊስ ባለፈው ረቡዕ ለሐሙስ አጥቢያ በመዲናይቱ ናይሮቢ የሚገኝ የአንድ የታወቀ ጋዜጣ ጽሕፈት ቤት ከመውረሩ ጎን የአንድ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሥርጭትንም ለጊዜው አቋርጦ ነበር። ይህ ዓይነቱ ርምጃ ኬንያ ነፃነት ካገኘች ካለፉት አርባ ዓመታት ወዲህ ተወስዶ ስለማያውቅ ጋዜጠኞችና ነዋሪዎች በድርጊቱ ተደናግጠዋል፤ ይሁንና፡ የመንግሥት ባለሥልጣናት በጉዳዩ ያን ያህል አልተጨነቁም። በሕገ መንግሥቱ ላይ የተካሄደው ሬፈረንደም ከከሸፈ እና የሙስና ቅሌቶችም ከወጡ በኋላ በፕሬዚደንት ሙዋይ ኪባኪ የሚመራው የኬንያ መንግሥት በወቅቱ ትልቅ ውዝግብ ውስጥ ገጥሞታል።