1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
መቅሰፍትአፍሪቃ

ኬንያ፦ በጎርፍ መጥለቅለቅ 91 ሰዎች የገቡበት ዐልታወቀም

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 22 2016

ኬንያ በሰሞነኛው የጎርፍ መጥለቅለቅ ቢያንስ 91 ሰዎች የገቡበት ዐልታወቀም ። የኬንያ የሕይወት አድን ሠራተኞች በጎርፍ የተወሰዱ ሰዎችን ለማግኘት የማፈላለግ ጥረታቸውን አጠናክረዋል ።በሰኞ ዕለቱ መጥለቅለቅ ብቻ ከ66 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል ። ከ190 ሺ በላይ የሚሆኑት ደግሞከቤት ቀዬያቸው ተፈናቅለዋል ።

https://p.dw.com/p/4fN3M