ኬንያዉያን ስደተኞች በኡጋንዳ | አፍሪቃ | DW | 17.01.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ኬንያዉያን ስደተኞች በኡጋንዳ

በኬንያ የምርጫ ዉጤት መጭበርበር ሰበብ የተቀሰቀሰዉን ቀዉስ ለማብረድ ተቀናቃኝ ፖለቲከኞችን ለመሸምገል ከአህጉሪቱም ሆነ ከአለም መንግስታት የተደረገዉ ጥረት እስካሁን ስኬት አላገኘም። የተቀናቃኝ ፓርቲዉ በራይላ ኦዴንጋ ወገን እና በአገሪቱ ፕሪዝዳንት በሞይኪባኪ ወገን የሚደረገዉ ግጭትን ሽስት በርካታ ኬንያዉያን ወደ ጎረቤት ኡጋንዳ በመሰደድ ላይ ናቸዉ

default

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ እንዳስታወቀዉ 6200 ያህል ስደተኞችን ከኬንያ ድንበር አዋሳኝ ወደ ሆነዉ የኡጋንዳ መንደር አመላልሶ እርዳታዉን በመለገስ ላይ ነዉ። በአንጻሩ የኡጋንዳ የእርዳታ እና ዝግጁነት ቢሮ እስካሁን የደረሰዉ እርዳታ በቂ አለመሆኑን በመግለጽ ላይ ይገኛል። የኡጋንዳ የጸጥታ ቢሮም በስደተኞቹ ካንፕ አስጊ የሆነ የጎሰኝነት ችግር መከሰቱን ገልጾአል። በሌላ በኩል በኬንያ ለዘመናት ይኖሩ የነበሩ ያህል የኡጋንዳ ስደተኞች ወደ ቀድሞ ቀያቸዉ እና ቤተ-ዘመዶቻቸዉ ተመልሰዋል። በዚህ ጉዳይ ዙርያ አዜብ ታደሰ ወደ ካንፓላ በመደወል የዶቸ ቬለ ዘጋቢ አሌክስ ጂተርን አነጋግራለች

ተዛማጅ ዘገባዎች