ካርኒቫል በጀርመን | ባህል | DW | 02.03.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ካርኒቫል በጀርመን

ካርኒቫል Carne Vale ከተሰኙ ሁለት የላቲን ቃላት የተዋቀረ ሲሆን፤ትርጓሜውም “ስጋ ደህና ሰንብት” እንደማለት ነው ይላል አንድ ጥናታዊ ፅሁፍ። ካርኒቫል አብዛኛውን ጊዜ ጀርመንን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮጳ ሀገራት በካቶሊክ ክርስቲያኖች እና በምስራቅ ኦርቶዶክሶች ዘንድ ተዘውትሮ የሚከበር ነው።

የካርኒቫል ታዳሚያን በጎዳና

የካርኒቫል ታዳሚያን በጎዳና

የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን ልብስ የሙጥኝ ብለው በአየር ላይ ሲንሳፈፉ ታይተዋል። ዋነኞቹ የጀርመን የፖለቲካ ፓርቲዎች CDU እና SPDም የቡጢ መድረክ ተዘጋጅቶላቸው ጓንቶቻቸውን አጥልቀው ተፋጠዋል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ታዳሚያንም በምዕራብ ጀርመን የNord Rhein Westfalen ግዛት ውስጥ በሚገኙ ከተሞች ግልብጥ ብለው ተጎዳና ተ ገኝተዋል። ሰዉ የጎዳና ላይ ካርኒቫሉን የፖለቲካ፣ የማኍበራዊና የምጣኔ ሀብታዊ ስላቅ ሲያንጸባርቅበት ታይሮዋል።