ካርቱም፥-የሱዳኖች ጦርነት ተባብሷል | አፍሪቃ | DW | 11.04.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ካርቱም፥-የሱዳኖች ጦርነት ተባብሷል

በአዲስ አበባ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጦራቸዉ ሒጂሊጅን የተቆጣጠረዉ የሰሜን ሱዳን ጦር ተኩስ ሥለከፈተበት ነዉ።የሰሜን ሱዳን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ራሕማ መሐመድ ኦስማን እንዳስታወቁት ደግሞ የጁባ ጦር የሰሜን ሱዳንን ሰባ ኪሎ ሜትር ግዛት ወሯል።

የሰሜንና የደቡብ ሱዳን መንግሥታት ጦሮች በሁለቱ ሐገራት አዋሳኝ ድንበር ላይ የገጡሙት ዉጊያ ብሶ ቀጥሏል።የካርቱምና የጁባ ባለሥልጣናት ሕዝባቸዉ ከየጦሩ ጎን እንዲቆም በየፊናቸዉ እየጠየቁ ነዉ።የሰሜን ሱዳን መንግሥት ዛሬ እንዳስታወቀዉ የደቡብ ሱዳን ጦር፥ በደቡብ ሱዳን የሚደገፈዉ SPLA-N በሚል ምሕፃረ-ቃል የሚጠራዉ አማፂ ቡድንና ጂም በሚል አፅሕሮቱ የሚጠራዉ የዳርፉር አማፂ ቡድን ለሰወስት ጥቃት ከፍተዉብኛል በማለት ይወነጅላል።ሁለቱ አማፂ ቡድናት ግን በዉጊያ አልተሳተፍንም ባይ ናቸዉ።ዛሬ እንዳዲስ ባገረሸዉ ዉጊያ ባለፈዉ ሐምሌ ከሰሜን ሱዳን የተገነጠለችዉ የደቡብ ሱዳን ጦር ሒጂሊጅ የተባለዉን የሰሜን ሱዳን ግዛትና ባካባቢዉ የሚገኘዉን የነዳጅ ጉርጓድ ተቆጣጥሮታል።በአዲስ አበባ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር አሮፕ ዴንግ ኩኦል እንደሚሉት ጦራቸዉ ሒጂሊጅን የተቆጣጠረዉ የሰሜን ሱዳን ጦር ተኩስ ሥለከፈተበት ነዉ።«ትናንት ሐይላቸዉን ከሒጂሊጅ ወደ ደቡብ ሱዳን አንቀሳቅሰዉ ነበር።የደቡብ ሱዳን መከከላከያ ሐይል በወሰደዉ አፀፋ ጥቃት፥ ጥቃቱን አክሽፎ ወደ ሒጅሊጅ መልሷቸዋል።ከሒጅሊጅ ከተማም አባርሯቸዋል።ሥለዚሕ ባሁኑ ሰዓት የደቡብ መከላከያ ሐይል ሒጅሊጅን እየተቆጣጠረ ነዉ።»

የሰሜን ሱዳን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ራሕማ መሐመድ ኦስማን እንዳስታወቁት ደግሞ የጁባ ጦር የሁለቱን ሐገራት አዋሳኝ ድንበር አልፎ የሰሜን ሱዳንን ሰባ ኪሎ ሜትር ግዛት ወሯል።ሚንስትሩ አክለዉ እንዳሉት ካርቱም ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ለአፍሪቃ ሕብረት አቤቱታ አቅርባለች።የካርቱም መንግሥት ጦር ግን የተያዘበትን ግዛት በሐይል እንደሚያስለቅቅ እየዛተ ነዉ።የአፍሪቃ ሕብረት የሱዳኖችን ዉጊያ በጣም አሳሳቢ ብሎታል። ጌታቸዉ ተድላ ሃይሌ ጊዮርጊስ አምባሳደር ኩኦልን በስልክ አነጋግሮ የሚቀጥለዉን ዘገባ አዘጋጅቶአል።

ጌታቸዉ ተድላ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች