ካርልሐይንስ በም ተቀበሩ | ዓለም | DW | 13.06.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

ካርልሐይንስ በም ተቀበሩ

ከ1980ዎቹ ጀምሮ ሜንሽን ፉር ሜንሽን የሚል ግብረ-ሠናይ ድርጅት መሥርተዉ ብዙ ሺሕ ኢትዮጳዉያንን በመርዳታቸዉም ምስጋና፤ አድናቆትና ዕዉቅናን ያገኙ በጎ አድራጊ ግለሰብ ነበሩ።86 ዓመታቸዉ ነበር።

ባለፈዉ ግንቦት ሃያ-አንድ ያረፉት ኦስትሪያዊዉ የፊልም ተዋኝና ታዋቂ በጎ አድራጊ ካርል ሕይንስ በም ዛልስቡርግ-ኦስትሪያ ዉስጥ ዛሬ ተቀበሩ።በቀብር ሠነ-ሥርዓቱ ላይ ቤተ-ሠቦቻቸዉ፤ ከአራት መቶ የሚበልጡ የመንግሥት ባለሥልጣናት፤ ጓደኞቻቸዉና ወዳጆቻቸዉ ተገኝዋል።በም የተሸኙት የቀድሞዉ የጀርመን ርዕሠ-ብሔር ሆርስት ከለር ባደረጉት ንግግር ነዉ።በ1950ዎቹ በተጫወቱት ዚሲ በተሰኘዉ የፍቅር ፊልም ሥምና ዝና ያተረፉት በም፤ ከ1980ዎቹ ጀምሮ ሜንሽን ፉር ሜንሽን የሚል ግብረ-ሠናይ ድርጅት መሥርተዉ ብዙ ሺሕ ኢትዮጳዉያንን በመርዳታቸዉም ምስጋና፤ አድናቆትና ዕዉቅናን ያገኙ በጎ አድራጊ ግለሰብ ነበሩ።86 ዓመታቸዉ ነበር።የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል አጭር ዘገባ አለዉ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic