ካራቱሪ ኩባንያ የቀረበበት አቤቱታ | ኢትዮጵያ | DW | 09.05.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ካራቱሪ ኩባንያ የቀረበበት አቤቱታ

ካራቱሪ የተባለዉ የህንድ ኩባንያ ጋምቤላ ዉስጥ ለእርሻ ሥራ የተሰጠዉን አንድ መቶ ሺህ ሄክታር መሬት ማልማትን ትቶ ከቀረጥ ነፃ የገቡ ማሽኖችን በማከራየት ሥራ መጠመዱን ሠራተኞች አመለከቱ።

Landverpachtung an ausländische Investoren in Äthiopien

ድርጅቱ ከ2000ዓ,ም ጀምሮ ከሰባት መቶሄክታር በላይ ጥቅጥቅ ደን በመመንጠር 20 ሺህ ኩንታል በቆሎ ካመረተ በኋላ ቀሪ ጊዜዉን ማሽን በማከራየት ተግባር መጠመዱ ተገልጿል። ኩባንያዉ በርካታ ሠራተኞቹን ከማባረሩ በተጨማሪ ደሞዝ ለመክፈልም ብዙ ደጅ ጥናት መኖሩን ከድርጅቱ ሠራተኞች ለዶቼ ቬለ ዘጋቢ ለዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር በዝርዝር ገልጸዋል።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር፣

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic