ካለስምምነት የተበተነው የደቡብ ሱዳን ድርድር | አፍሪቃ | DW | 06.03.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ካለስምምነት የተበተነው የደቡብ ሱዳን ድርድር

ዛሬ ከአግባቢ ሥምምነት ይደርሳል ተብሎ የነበረዉ የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ሃይሎች የሰላም ድርድር ያለ ስምምነት ተጠናቀቀ። የሰላም ድርድሩ ከምን እንደደረሰ እና መቼ እንደሚቀጥል እሳካሁን በግልፅ የታወቀ ነገር የለም።

በአዲስ አበባ ሲካሄድ የነበረው የደቡብ ሱዳን መንግስት እና የአማጽያን ድርድር ያለምንም ስምምነት ተቋርጧል። በፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር እና ተቀናቃኛቸው ሪየክ ማቻር መካከል ሲካሄድ የነበረው ድርድር መቼ እንደሚቀጥል እንደማይታወቅ ሬውተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ድርድሩን በበላይነት የሚመራዉ የምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በጉዳዩ ላይ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።ተፋላሚ ኃይላት መሪዎች ሥምምነት እንዲፈራረሙ ኢጋድ የቆረጠዉ ቀነ ገደብ ትናንት ቢጠናቀቅም ድርድሩ ከተዘጉ በሮች ጀርባ ዛሬም ቀጥሎ ነበር።ሁለቱ ተቀናቃኝ ሃይሎች ካሁን ቀደም በተቀመጡ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ስለመድረሳቸው የተሰማ አንዳች ነገር የለም። በኢትዮጵያየሰላምናየልማትዓለምዓቀፍተቋምየምሥራቅአፍሪቃጉዳዮችየፖለቲካተንታኝአቶአቤልአባተ የፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር እና የሪየክ ማቻር ልዩነት እና የስልጣን ክፍፍል ጉዳይ አሁንም መፍትሄ አለማግኘቱን ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር የቀድሞ ምክትላቸውን ሪየክ ማቻርን ሐቻምና ሐምሌ ከስልጣን ካባረሩ እና አንዳቸው በሌላቸው ላይ ነፍጥ ካነሱ በኋላ በየምሥራቅአፍሪቃየልማትበይነ-መንግስታትባለሥልጣን የበላይነት የተጀመረው ድርድር ጉዳዩን በቅርበት ለሚከታተሉ ሁሉ ተስፋ አስቆራጭ ሆኗል። የድርድሩን ሂደት በሚያስተጓጉሉ የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ላይ ዓለም አቀፍ የጉዞ እና ሃብታቸውን ከማንቀሳቀስ የሚያግደው ማዕቀብ ለመጣል የቀረበው ሃሳብ ከሌላ ጊዜ በተለየ ዩናይትድ ስቴትስን ከቻይናና ሩሲያ ጋር ማስማማቱ ትርጉም እንዳለው አቶ አቤል አባተ ያምናሉ።

ከዚህ በተጨማሪ በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሌ ሴንጎን ኦባሳንጆ የሚመራው የደቡብ ሱዳን አጣሪ ኮሚሽን አገሪቱ በአፍሪቃ ህብረት የሞግዚት አስተዳደር ስር እንድትቆይ ሃሳብ ማቅረቡን ሬውተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። አጣሪ ቡድኑ የአሁኑን የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር እና ተቀናቃኛቸውን ሪየክ ማቻርን ከሽግግር መንግስቱ ውጪ የማድረግ ሃሳብ መሰንዘሩን የዜና ወኪል ጨምሮ ዘግቧል።አቶ አቤል አባተ ሉዓላዊቷ ደቡብ ሱዳን ላይ እንዲህ አይነት ውሳኔ መወሰን አስቸጋሪ መሆኑን ይናገራሉ።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት የቀረበው የማዕቀብ ሃሳብ የጦር መሳሪያ ግዢን እስከማገድ እና የከፍተኛ ባለስልጣናትን ዝዉዉርን እስከ መንፈግ ሊደርስ ይችላል ተብሏል።የደቡብ ሱዳን አጣሪ ኮሚሽን የሰላም ድርድሩን የሚያደናቅፉ የተባሉትንና የጉዞ እና የሃብት እገዳ ማዕቀቡ የሚመለከታቸውን ግለሰቦች የመለየት ሃላፊነት ተጥሎበታል።

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic