1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሱ የብሪታንያ ጠ/ሚ ሰር ኪየር ስታርመር ማን ናቸው?

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 2 2016

58ኛ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው የተመረጡት ሰር ኪየር ስታርመር በአገሪቱ ፖለቲካ የገነነ ስም የላቸውም ። እንዲያም ሆኖ ግን ወደ ከፍተኛ ሥልጣን ማማ ላይ መውጣታቸው ብዙዎችን አስገርሟል። ለመሆኑ ኪየር ስታርመር ማን ናቸው?

https://p.dw.com/p/4i3Lt
Nach den Parlamentswahlen in Großbritannien
ምስል Chris Eades/dpa/picture alliance

ለመሆኑ ኪየር ስታርመር ማን ናቸው?

58ኛ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው የተመረጡት ሰር ኪየር ስታርመር በአገሪቱ ፖለቲካ የገነነ ስም የላቸውም ። እንዲያም ሆኖ ግን ወደ ከፍተኛ ሥልጣን ማማ ላይ መውጣታቸው ብዙዎችን አስገርሟል። ለመሆኑ ኪየር ስታርመር ማን ናቸው? 

ከብዙ ዓመት የሰብአዊ መብት ሕግ ባለሞያ አገልግሎት በኋላ በ52 ዓመት እድሜያቸው ወደ ፓርቲ ፖለቲካ የመጡት ሰር ኪየር ስታርመር እድሜያቸውን በሙሉ በሰብአዊ የሕግ ተሟጋችነት ያሳለፉ ናቸው።

አኤክስተር በተባለ ከለንደን ወጣ ባለ ሰሪ ወረዳ እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር መስከረም 2 ቀን፣ 1962 ዓ.ም የተወለዱት ስታርመር አባታቸው የፋብሪካ ሠራተኛና እናታቸው ደግሞ የሆስፒታል ነርስ ነበሩ ። ሰር ኪየር ትምህርታቸውን እንደማንኛውም ከዝቅተኛ ቤተሰብ የመጣ ልጅ በሕዝብ ትምህርት ቤት የተከታተሉ ሲሆን፤ ከፍተኛ ነጥብ በማምጣትም ከዘመዶቻቸው ሁሉ የመጀመርያው በመሆን ሊድስ ዩኒቨርሲቲ በመግባት በ1987 ዓ.ም እንደ አውሮጳውያኑ አቆጣጠር በሕግ ሞያ ተመርቀዋል ። የብሪታንያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ያልተጠበቀ መግለጫ

ሰር ኪየር አብዛኛውን ጊዜያቸውን ከተመረቁ በኋላ ነፃ የሕግ ማማከር አገልግሎት ለደሀና ለተጎዱ ሰዎች ለብዙ ጊዜ ሲሰጡ ቆይተዋል ። ከዚያም በደረጃው ከፍ ያለ ሥፍራ የሚሰጠው የሰሜን አየርላንድ የፖሊሲ ቦርድ አማካሪ ሆነው ለመጀመርያ ጊዜ ሠርተዋል። በዚህ ሥራቸው የስቅለተዓርብ ተብሎ በሚታወቀው ብሪታንያ እና በሰሜን አየርላንድ መካከል በተደረገው የተሳካ የሰላም ስምምነት ሰር ኪየር ላደረጉት አስተዋፅኦ ከፍተኛ ዕውቅናን አስገኝቶላቸዋል።

ሰር ኪየር በ2007 ያገቧቸው ባለቤታቸው ወ/ሮ ቪክቶሪያ ስታርነር የዚሁ ሰሜን አየርላንድ ተወላጅ ናቸው። ቪክቶሪያ የህክምና ባለሞያ ነርስ ሲሆኑ ሁለት ልጆችም በጋራ አፍርተዋል። በ2008 ሰር ኪየር የጠቅላይ አቃቤ ሕግ ሁነው ተሹመዋል። በዚህ ሥራቸ ብዙ የተቸገሩና መድሎ የደረሰባቸውን ሰዎች የረዱ ሲሆን፤ በዘረኝነት በግፍ የተገደለው ታዋቂው ወጣት ስተቨን ሎውረንስ ገዳዮች ለፍርድ እንዲቀርቡም አድርገዋል።

የሰሜን አየርላንድ የፖሊሲ ቦርድ አማካሪ ሆነው ለመጀመርያ ጊዜ ሠርተዋል
ሰር ኪየር ስታርመር ከተመረቁ በኋላ ነጻ የሕግ ማማከር አገልግሎት ለደሀና ለተጎዱ ሰዎች ለብዙ ጊዜ ሲሰጡ ቆይተዋል ። ከዚያም የሰሜን አየርላንድ የፖሊሲ ቦርድ አማካሪ ሆነው ለመጀመርያ ጊዜ ሠርተዋልምስል Stefan Rousseau/empics/picture alliance

ሰር ኪየር ወደ ፓርቲ ፖለቲካ የመጡት በሕዝብ ተወዳጅ የሆኑት  የሠራተኛው ፓርቲ መሪ የነበሩት ጀርሚ ኮርቢን የፓርቲው መሪ ከሆኑ በኋላ ባደረጉላቸው ጥሪ መሰረት በ2015 ነው ። ከዝያም በፓርቲ ውስጥ «ሻዶው» ወይም ጥላ ተብሎ በሚጠራው የሚንስትርነት ቦታዎች አገልግለዋል ።

ከ2019 የሠራተኛው ፓርቲ ጠቅላላ ሽንፈት በኋላ በ2020 የፓርቲው መሪ ሆነው ተመርጠዋል። በመጨረሻም ከ1997 የቶኒ በሌየር ሙሉ በሙሉ ድል በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ሰር ኪየር በሐምሌ 4 ቀን፣ 2024 ዓ.ም 58ኛው የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተነርጠዋል ።

መኮንን ሚካኤል

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ፀሐይ ጫኔ