ኪንጄኬቲሌ፥ የታንዛኒያ የነጻነት ተጋድሎ ፈር ቀዳጅ | ራድዮ | DW | 05.04.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ራድዮ

ኪንጄኬቲሌ፥ የታንዛኒያ የነጻነት ተጋድሎ ፈር ቀዳጅ

ኪንጄኬቲሌ ንጓሌ በአፍሪቃ ታሪክ አወዛጋቢ ሥፍራ አላቸው። በ20ኛው ክፍለ-ዘመን መባቻ አኹን ታንዛኒያ ብለን የምንጠራት ሀገር ዜጎች የጀርመን ቅኝ ገዢዎችን ተቃውመው እንዲታገሉ አበረታትተዋል። ተከታዮቻቸው ጥይት እንዳይመታቸው የሚጋርድ የተቀደሰ ውኃ አለኝ ሲሉ ቃል በመግባታቸውም ይታወቃሉ። አንዳንዶች ኪንጄኬቲሌን ለሕዝባቸው ተስፋ እና ብርታትን ያሰነቁ ጀግና አድርገው ይመለከቷቸዋል። ሌሎች ደግሞ ሰውዬው ሕዝባቸውን ወደ ሞት የነዱ አታላይ ነበሩ ይሏቸዋል።#ARAMH

ቪድዮውን ይመልከቱ። 01:47