ኪስማዩና የሶማሊያ ተፋላሚ ኃይሎች | አፍሪቃ | DW | 19.09.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ኪስማዩና የሶማሊያ ተፋላሚ ኃይሎች

የሶማሊያው ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አሸባብ ከመቅዲሾ በስተደቡብ ከምተገኘዋ ከኪስማዩ ካፈገፈገ ቀናት ተቆጥረዋል ። ይሁንና ከተማይቱ እስከ ዛሬ በአፍሪቃ ህብረት ኃይል በሚደገፈው በሶማሊያ መንግሥት ወታደሮች እጅ አልገባችም ። የመቅዲሾ የዶቼቬለ ወኪል አዌስ ሁሴን እንዳለው አሁን በከተማይቱ የአስተዳደር ክፍተት ተፈጥሯል ።

የሶማሊያው ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አሸባብ ከመቅዲሾ በስተደቡብ ከምተገኘዋ ከኪስማዩ ካፈገፈገ ቀናት ተቆጥረዋል ። ይሁንና ከተማይቱ እስከ ዛሬ በአፍሪቃ ህብረት ኃይል በሚደገፈው በሶማሊያ መንግሥት ወታደሮች እጅ አልገባችም ። የመቅዲሾ የዶቼቬለ ወኪል አዌስ ሁሴን እንዳለው አሁን በከተማይቱ የአስተዳደር ክፍተት ተፈጥሯል ። ነዋሪዎችም ከተማይቱን ለቀው እየሄዱ ነው ። 

ደቡብ ሶማሊያ የምትገኘው የወደብ ከተማ ኪስማዩ ለሶማሊያው ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አሸባብ ደቡባዊ ዘመቻዎች በማዕከልነት የምታገለግል ቁልፍ ከተማ ነበረች ። አሸባብ ከዚህች ከተማ ያፈገፈገው መቅዲሾ የሚገኘው የዶቼቬለ ወኪል አዌስ ሁሴን እንዳለው በአሚሶምና በሶማሊያ ወታደሮች ከባድ ኪሳራ ከደረሰበት በኋላ ነው ።

« ከኪስማዩ ውጪ ከባድ ውጊያ ነበር በዚህ ውጊያ ትልቁ ምሽጋቸው በአሚሶምና በሶማሊያ ወታደሮች ወድሟል ።ጠንካራ ይዞታቸው ከተደመሰሰ በኋላ ነው ከተማይቱን ለቀው መውጣት የጀመሩት ። »

ትንንት በወጡ ዘገባዎች መሰረት አሸባብ አዛዦቹን ከኪስማዩ አስወጥቶ እግረኛ ተዋጊዎችን እዚያው ትቷል ። አዌስ ሁሴን እንደሚለው አሸባብ ኪስማዩን ለቆ የወጣው ከ3ቀናት በፊት ቢሆንም እስከ ዛሪ ከሰአት በኋላ ድረስ ከተማይቱን የያዘ ኃይል የለም ።

«ከኪስማዩ የምንሰማው ዜና ፣ የአሸባብ ኃይሎች ከ 3 ቀናት በፊት ከከተማይቱ ሸሽተው ኪስማዩ ዙሪያ ወደ ሚገኙ አካባቢዎች በተለይም ወደ ሰሜን ኪስማዩ አካባቢ እንደሄዱ ነው የሚጠቁመው ። በአፍሪቃ ህብረት ሰላም አስከባሬ ኃይል አሚሶም የሚደገፉት የሶማሊያ መንግስት ወታደሮች እስካሁን ከተማይቱ አልገቡም ። ያሉት ከከተማይቱ ውጭ ነው ። በከተማዋ አሁን የአስተዳደር ክፍተት አለ »

ይህ የአስተዳደር ክፍተትም እንደ አዌስ ነዋሪዎችን ስጋት ውስጥ ከቷል ። በዚህ ሰበብ በርካታ የከተማይቱ ነዋሪዎች ወደ ሌላ አካባቢ ሸሽተዋል ። በአዌስ አባባል በኪስማዩ ለህዝቡ የእለት ተለት ኑሮ አሰፈላጊ የሆኑ እንቅስቃሴዎች የሉም ።

«ነዋሪዎች በተፈጠረው የአስተዳደር ክፍተት ስጋት ላይ ነን ያላሉ ። የሚያስተማምን ነገር የለም ። ዝርፊያ አለ ። ከተማይቱን የሚቆጣጠር ስለሌለ አንዳንድ ዝርፊያ ይካሄዳል ። የንግድ እንቅስቃሴ የለም ። ሁሉም ነገር ቆሟል ። ከተማይቱን የሚያስተዳድር ባለመኖሩ ሰላማዊ ሰዎች ከተማይቱን ለቀው እየወጡ ነው ።»

አሸባብ ከኪስማዩ ከወጣ ሶስት ቀናት ከተቆጠረና የአስተዳደር ክፍተትም መፈጠሩ ከታወቀ ፣ የሶማሊያ መንግሥት ወታደሮች ከተማይቱን ያልያዙበት ምክንያት ምን ይሆን ? ለአዌስ ያቀረብኩት ጥያቄ ነበር ።

«ይህ  በኪስማዩና አካባቢው የሚኖሩ ሰዎች ርስ በርስ የሚጠያያቁት ጉዳይ ነው ። ከ3 ቀናት አንስቶ የአስተዳደር ክፍተት አለ ። ሆኖም ኪስማዩ የሚገኝ ዘጋቢ እነዚህ ኃይሎች በሰዓታት ውስጥ ወደ ከተማይቱ ለመግባት እየሞከሩ መሆኑን ተናግሯል »

አሸባብ ከጠንካራ ይዞታው ከኪስማዩ ቢወጣም አሁንም በቁጥጥሩ ስር ያሉ ሌሎች አካባቢዎች አሉ ። አዌስ እንዳለው ከነዚህ መካከል በመካከለኛው ጁባ ያሉት ጃማማና ጃሊብ ይገኙበታል ። አሸባብ ኪስማዩን ለቆ መውጣቱ እንደ ትልቅ ሽንፈት ተወስዷል ። ይሁንና በደፈጣ ጥቃቱ መቀጠሉ በብዙዎች ግምት አያጠያይቅም  ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic