ከ60 በላይ ሲቪል ማሕበራት የመቀሌ ጉብኝት | ኢትዮጵያ | DW | 23.01.2023
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ከ60 በላይ ሲቪል ማሕበራት የመቀሌ ጉብኝት

ከ60 በላይ የኢትዮጵያ ሲቪል ማሕበራት እንዲሁም የሌሎች ተቋማት ተወካዮች ዛሬ በመቐለ ተገኝተው ከትግራይ ክልል ሲቪል ተቋማት አመራሮች ጋር ተወያዩ። የተቋማቱ የዛሬ የመቐለ ጉብኝት በጦርነቱ ምክንያት ለሁለት ዓመት ተቋርጦ የቆየ ማእከላቸው አዲስአበባ እና መቐለ ያደረጉ የሲቪል ተቋማት ግንኙነት ዳግም ያስጀመረ ተብሎለታል።

ሲቪል ተቋማት ግንኙነትን ዳግም ያስጀመረ

ከ60 በላይ የኢትዮጵያ ሲቪል ማሕበራት እንዲሁም የሌሎች ተቋማት ተወካዮች ዛሬ በመቐለ ተገኝተው ከትግራይ ክልል ሲቪል ተቋማት አመራሮች ጋር ተወያዩ። የተቋማቱ የዛሬ የመቐለ ጉብኝት በጦርነቱ ምክንያት ለሁለት ዓመት ተቋርጦ የቆየ ማእከላቸው አዲስአበባ እና መቐለ ያደረጉ የሲቪል ተቋማት ግንኙነትን ዳግም ያስጀመረ ተብሎለታል።

የኢትዮጵያ ሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ምክርቤት ያስተባበረው እና በርካታ የኢትዮጵያ ሲቪል ተቋማት የተሳተፉበት ዛሬ በመቐለ ከትግራይ አቻ ተቋማት ጋር የተደረገው ውይይት እና የስራ ጉብኝት በጦርነቱ ምክንያት ለሁለት ዓመታት ተቋርጦ የቆየው የሁለቱ ወገን የሲቪል ተቋማት ግንኙነት ዳግም ያስጀመረ ተብሎለታል። 61 የተለያዩ የኢትዮጵያ ሲቪል ተቋማት ተወካዮች ከአዲስአበባ መቐለ በመምጣት በትግራይ ካሉ ከ72 በላይ የሲቪል ተቋማት ተወካዮች ጋር የተገናኙበት የዛሬው መድረክ፥ የተለያዩ የማሕበረሰብ ክፍሎች የሚወክሉ ተቋማት ግንኙነት ከማስቀጠል በተጨማሪ በጦርነቱ ምክንያት እንቅስቃሴያቸው ተገትቶ የነበሩ ድርጅቶች ዳግም ስራ የሚጀምሩበት ሁኔታ ለመፍጠር፣ አጋርነት ለማሳየት እንዲሁም የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት ስራዎች ለማጠናከር ያለመ መሆኑ በአዘጋጆቹ በኩል ተገልጿል።

Äthiopien Tigray l Treffen der äthiopischen Zivilorganisationen in Mekele

ከ60 በላይ የኢትዮጵያ ሲቪል ማሕበራት እንዲሁም የሌሎች ተቋማት ተወካዮች በመቐለ

በሲቪል ተቋማቱ የመቐለ ጉብኝት ያነጋገርናቸው የኢትዮጵያ ሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ምክርቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሄኖክ መለሰ፣ በጦርነቱ ምክንያት የተጎዳ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በማጠናከሩ ረገድ ሲቪል ተቋማት ከፍተኛ ሚና አላቸው ያሉ ሲሆን ይህ ሚና ለመወጣት በትግራይ ካሉ አቻ ማሕበራት ጋር ይሰራል ብለዋል።
የትግራይ ሲቪል ተቋማት ሕብረት ስራ አስኪያጅ አቶ ያሬድ በርሃ በበኩላቸው የ61 ተቋማቱ የመቐለ ጉብኝት እና ከመሰል ተቋማት ያደረጉት ውይይት ፍርያማ ነበር ያሉት ሲሆን በተለይም በሰላም ግንባታ፣ ሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ላይ ትኩረት ተደርጎ ሊሰራ ይገባል ብለዋል። ዛሬ በመቐለ የተገኙት የ61 ሲቪል ተቋማት ተወካዮቹ በከተማው የሚገኝ የተፈናቃዮች መጠልያ ጣብያ እና ፌስቱላ ማእከላት ጎብኝተዋል።

 

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ 

አዜብ ታደሰ 

ታምራት 

Audios and videos on the topic