ከ40 ዓመት በፊት በ60 ሹማማንት ላይ የተፈጸመ አስደንጋጭ ድርጊት | ኢትዮጵያ | DW | 24.11.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ከ40 ዓመት በፊት በ60 ሹማማንት ላይ የተፈጸመ አስደንጋጭ ድርጊት

«ያለምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም» የሚል መዝሙር እየዘመረ ፣ አዝጋሚ የተሰኘውን አብዮት የመራው ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ)፣ ንጉሡን ከሥልጣን ባስወገደ በ 2 ወር ከ 2 ሳምንት ፣ መሪ መፈክሩን መለወጡ የሚታወስ ነው።

ኅዳር 14 ,1967 ዓ ም፤ 60 የአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ፤ የሲቭልና የጦር ኃይል ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ፤ በአንድ ምሽት ረሸነ። ድርጊቱም፤ በአብዮቱ ሰላማዊ ለውጥ ተካሄዷል ብሎ ሂደቱን ያደንቅ የነበረውን የኢትዮጵያን ሕብረተሰብና የዓለምን ማሕበረሰብ ማስደንገጡ አይዘነጋም። ያ ድርጊት በኢትዮጵያ ታሪክ ያስከተለውን ሁኔታ ከታዘቡት መካከል ፤ በቤልጅግ ኑዋሪ የሆኑትን የፖለቲካና ኤኮኖሚ ምሁር አቶ አበራ የማነ አብንን በስልክ አነጋግረናል።

ተክሌ የኋላ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic