ከ40ዓመት በኋላ የታየዉ የጉንፋን ወረርሽኝ | ጤና እና አካባቢ | DW | 16.06.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

ከ40ዓመት በኋላ የታየዉ የጉንፋን ወረርሽኝ

የዓለም የጤና ድርጅት H1N1 ቫይረስ ያስከተዉን ጉንፋን መንግስታት በተጠንቀቅ ሆነዉ እንዲከላከሉ መልዕክቱን አስተላልፏል።

default

H1N1 ቫይረስ

ድርጅቱ ምንም እንኳን የበሽታዉ ሁኔታ ከደረጃ አምስት ወደደረጃ ስድስት ከፍ ማለቱን ቢናገርም ሰዎች ከቁጥጥር ዉጪ ሆኗል የሚል ስጋት እንዳያድርባቸዉ አሳስቧል። በጉንፋኑ የተያዙች ሰዎች ቁጥርና በህይወት ላይ እያደረሰ ያለዉ ጉዳትም የሚጋነን አለመሆኑ ተገልጿል።

የአፍሪቃ የህክምና ምሁራን ፍልሰት

በሌላ በኩል አፍሪቃ በከፍተኛ ደረጃ የተማረ የሰዉ ኃይሏን እያጣች መሄዷ፤ ከምን በላይ ደግሞ ከጤናዉ ዘርፍ የሚሰደደዉ ባለሙያ ቁጥሩ እየበረከተ መሄዱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ያመላከተ ጥናት ባለፈዉ ሰሞን እዚህ ጀርመን ላይፕሲሽ ከተማ በተካሄደ ጉባኤ ላይ ተነስቶ ብዙ አነጋግሯል።

AFP/DPA/ZPR

ሸዋዬ ለገሠ/አርያም ተክሌ