ከፍተኛ የበቆሎ ምርት ዉጤት በደቡብ አፍሪቃ  | አፍሪቃ | DW | 28.06.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ከፍተኛ የበቆሎ ምርት ዉጤት በደቡብ አፍሪቃ 

ደቡብ አፍሪቃ በ 36 ዓመት ታሪኳ ከፍተኛ የተባለዉን የበቆሎ ምርት ማግኘትዋን አስታወቀች።  ኢሊኒኞ የተባለዉ የተፈጥሮ ክስተት በሚያስከትለው የአየር መዛባት  ባመጣዉ የአየር ጠባይ ለዉጥ ምክንያት ባለፉት ሁለት ዓመታት ድርቅእና የሰብል እጥረት  አጋጥሟታል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:17

ከድርቅ ማግስት በሀገሪቱ ከፍተኛዉ ምርት ታፍሷል፤

በወቅቱም ደቡብ አፍሪቃ ከተለያዩ ሃገራት የበቆሎ ምርትን መግዛትዋ ይታወቃል። ከፍተኛ የበቆሎ አምራችና ተጠቃሚ መሆንዋ የሚነገርላት ደቡብ አፍሪቃ የደረሰባትን የምግብ እጥር ችግር ለመቅረፍ ባደረገችዉ ትግል ታሪኳን መቀየርዋ ተሳክቶላታል። የገጸ- ምድርም ሆነ የከርሰ ምድር ዉኃ ሐብት ባለቤት የሆነችዉ ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪቃ ትምህርት መቅሰም እንደምትችል የግብርና ባለሙያዎች ጠቁመዋል። ከጆሃንስበርግ  ወኪላችን መላኩ አየለ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።   


መላኩ አየለ
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ   

Audios and videos on the topic