ከፍተኛ ትምህርትና ዘመናዊ ግብርና | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 17.09.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

ከፍተኛ ትምህርትና ዘመናዊ ግብርና

ባለፈው ኀሙስ፣ የርእሰ ዐውደ ዓመት ዕለት ወደ ራዲዮ ጣቢያችን ብቅ ብለው ከነበሩት በቦን ዩንቨርስቲ በከፍተኛ ደረጃ የግብርና ሳይንስ ትምህርት መከታተል ከጀመሩት 3 ኢትዮጵያውያን መካከል ፤ ከጂማ ዩንቨርስቲ የመጣው

ሐብታሙ ሥዩም -ኢትዮጵያ ፤ የተለያዩ አዝርእትን ፣ ፍራፍሬዎችንና ለምግብ የሚውሉ ቅጠላ ቅጠሎችን ለማምረት ፣ በተፈጥሮ ተስማሚ የሆነ የአየር ንብረት ያላት ሀገር ናት። የአየር ንብረቱ ክፉኛ እንዳይዛባ ፣ ተፈጥሮን በአግባቡ መንከባከብ ግድ ይላል። የሕዝብ ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ የምግብ ዋስትናን ይበልጥ አስተማማኝ ለማድረግ ፤ አርሶ አደሮች ለዘመናት ያካበቱትን ባህላዊ ዕውቀትም ሆነ ተመክሮ ከዘመናዊው ሳይንስ ጋር አጣምሮ ፣ ለዘመናዊ ግብርና መሥፋፋት መሥራት፣ ፋይዳ ይኖረዋል። የዘመናዊውን የግብርና ሳይንስ በከፍተኛ ደረጃ ፣ በነባቤ ቃልም በተግባርም ለመቅሰም ቦን ፤ ጀርመን ወደሚገኘው ዩንቨርስቲ ብቅ ያሉ 3 ኢትዮያውያን ተማሪዎችን አነጋግረናል ፣ የዛሬው ሳይንስና ሕብረተሰብ ዝግጅታችን ም በተጠቀሰው የግብርና ሳይንስ ላይ ይሆናል የሚያተኩረው።

ጀርመናውያን፣ ሁሉን ፣ በየዓይነቱና በየረድፉ፣ ግብርናውንም ሳይንሳዊ በሆነ አሠራር ማደራጀት አንዱ ጠንካራ ጎናቸው ነው። በቅርቡ ፣ ከኢትዮጵያ ወደዚህ አገር የመጡት የግብርና ሳይንስ ተማሪዎቹ ፣ ከጎንደር ዩንቨርስቲ የመጡት ፤ ፋጡማ ደገፋውና ተሾመ ወንዴ፤ እንዲሁም የጂማው ሐብታሙ ሥዩም ፣ እስካሁን ጀርመን ውስጥ ባዩት ምን እንደተሰማቸው ነበረ የጠየቅኳቸው

ግብርና ሠምሯል ማለት የሚቻለው፣ የተፈጥሮ አካባቢንም በመጠበቅ ጎን ለጎን ማስኬድ ሲቻል ነው። ኢትዮጵያውያን የዘመናዊ ግብርና ባለሙያዎች፤ አገራቸውን በዘመናዊ ግብርና መለወጥ፣ የምግብ ዋስትናንም አስተማማኝ ማድረግ እንደሚቻል ፣ ከ 40 ዓመትት ገደማ በፊት ፣ በተግባር አሳይተው ነበር። በ 2007 ና ወደፊትም ም ከዚያ የላቀ እንጂ የባሰ አይጠበቅም። የዛሬዎቹ እንግዶቼ ዘመናዊ የግብርና ሳይንስ ሰፊ ለውጥ ሊያስከትል እንደሚችል እነርሱም በዚህ ግብ ላይ ከማትኮር እንደማይቦዝኑ ገልጸውልኛል።

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic