ከፍተኛ ባለሥልጣናትን የሚመለከተው የገንዘብ ማሸሽ ቅሌት  | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 06.11.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ከፍተኛ ባለሥልጣናትን የሚመለከተው የገንዘብ ማሸሽ ቅሌት 

ከ67 ሀገራትየተውጣጡ 400 ጋዜጠኞች ይፋ ያደረጓቸው 13,4ሚልዮን ህቡዕ ሰነዶች በየሀገሮቻቸው ግብር እንዳይከፍሉ ሲሉ ገንዘባቸውን ወደውጭ ያሸሹ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናትን፣ ቱጃሮችንና የንግድ ተቋማትን ስም አጋለጡ። ፓራዳይዝ ፔፐርስ በሚል መጠሪያ ስር የወጡትን ሰነዶች ትናንት ያሾለከው የጀርመናውያኑ ዕለታዊ ዚውድዶይቸ ጋዜጣ ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:13
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:13 ደቂቃ

ፓራዳይዝ ፔፐርስ

ፓራዳይዝ ፔፐርስ በሚል መጠሪያ ስር  በወጡት ሰነዶች መሰረት፣ የገቢ ግብር ላለመክፈል በሚል  ገንዘባቸውን ቀረጥ ወደማያስከፍሉዋቸው ሀገራት አሸሽተዋል በሚል ስማቸው ከተጠቀሱት መካከል የእንግሊዝ ንግሥት ኤልሳቤጥ ዳግማዊት፣ የካናዳ ጠቅላይ ሚንስትር ጃስቲን ትሩዶ፣ የዩኤስ አሜሪካ የንግድ ሚንስትር ዊልበር ሮስ፣  ሌሎች የዩኤስ ካቢኔ አባላት ፣ ከአስር የሚበልጡ የፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አማካሪዎች እና በምርጫ ዘመቻ ገንዘብ የሰጡዋቸው  ግለሰቦች፣ እንዲሁም፣  ናይክ፣ አፕል፣ ፌስቡክ እና ኡበርን የመሳሰሉት የንግድ ተቋማት ይገኙባቸዋል።

መክብብ ሸዋ/አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ
 

Audios and videos on the topic