ከፊሉ የምርጫ ውጤት እና የመድረክ አስተያየት | ኢትዮጵያ | DW | 28.05.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ከፊሉ የምርጫ ውጤት እና የመድረክ አስተያየት

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ባለፈው እሁድ የተደረገውን ሀገራዊ ምርጫ ከፊል ውጤት፣ የምርጫው ሂደት ሰላማዊ አልነበረም በሚል አለመቀበሉን ገለጸ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 01:59
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
01:59 ደቂቃ

ከፊሉ የምርጫ ውጤት እና የመድረክ አስተያየት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከአራት ቀናት በፊት በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ እስካሁን ከክልሎች በደረሰው ከፊል ውጤት ገዢዉ ፓርቲ ኢ ህ አ ዴ ግ እና አጋር ድርጅቶች ለሕዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤቶች አብላጫዉን ድምፅ ማግኘታቸዉን በትናንቱ ዕለት መግለጹ ይታወቃል። በቦርዱ መግለጫ መሠረት፣ ኢ ህ አ ዴ ግ እና አጋር ድርጅቶች ከ547 የምክር ቤቶች መንበሮች 442 አግኝተዋል። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ፣ በምህፃሩ መድረክ ይህንኑ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያወጣውን ከፊል ውጤት፣ የምርጫው ሂደት ሰላማዊ አልነበረም በማለት እንደማይቀበለው ለዶይቸ ቬለ ገልጾዋል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic